🇿🇦🕯 የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሰራዊት በምሥራቅ ኮንጎ ጦርነት ቢያንስ 13 ወታደሮችን እንዳጣ ገለጸ
"ሰኞ ጥር 19 ቀን የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት የጦር ሰፈር በሚገኝበት የጎማ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጦር ሰራዊት፣ የኮንጎ መከላከያ ኃይል እና በኤም23 አማጺ ሚሊሻ መካከል በተደረገ የሞርታር ቦምብ ልውውጥ ሶስት የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሰራዊት አባላት ተገድለዋል" ሲል መግለጫው አስታውቋል።
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ ልዑክ እና በኮንጎ የተመድ ሰላም አስከባሪ ልዑክ አካል የሆነ አንድ የደቡብ አፍሪካ ወታደር ባለፉት ሶስት ቀናት ከኤም23 አማጺያን ጋር በተደረገ ውጊያ በደረሰበት ጉዳት ህይወቱ ማለፉን መግለጫው አክሏል።
ከኤም23 አማፂ ቡድን ጋር በተደረገ ከፍተኛ ውጊያ 9 ወታደሮችን እንዳጣ የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሰራዊት እሁድ እለት አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa