"መሃሙድና ትዝታ እዚህ ቦታ አረፍ ብለው ነበር"
... ከዕለተ እሁድ ረፋድ የፀሃይ እግሮች ጋር ማህሙድ ይራመዳል... ርጥብ ፀጉሩን እያደራረቀ የሬዲዮውን ድምፅ ጨመረው...
"... የፍቅር ወጥመድ ነው መላው ሁሉ ገላሽ
ምክንያት አጣሁኝ በምን ሰበብ ልጥላሽ..."
... ልቡ ውስጥ ካለው ሰላም ጋር ይደንሳል ... ከናፍቆቷ ጋር አብሮ ያዜማል... ስልኩን አውጥቶ መቅዳት ጀመረ
"... በፅጉርሽ እንዳይሆን ራስሽ ላይ ያለው
ሰው ይስቅብኛል ሃር ተወዳጅ ነው..." መልዕክቱን ላከላት...
አጭር "እንዴት አደርሽልኝ " አስከትሎ...
ትንሽ ቆይቶ የድምፅ መልዕክት ገባለት...
" ...የሆንክ ሽማግሌ... እኔ ይሄን ዘፈን አልወደውም..."
"... አንዴ ለምን..."
"... አሃ ሰበብ ቢያገኝ ሊጠላት አይደል..."
"😂😂😂"
"... ምን ያስቃል እውነቴ ነው..."
"... "እዎድሻለው" ማለት አፍሮ ነው..."
... የፈረሰ ቤታቸው ፍራሽ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠዋል... የሚበራ ነገ የላቸውም... ዛሬ ላይ ሊሞቱ ተቀጣጥረው ...
" ... እስኪ ዝፈንልኝ..."
"...ምን..."
"... ደስ ያለህን..."
"... ማን ብዬ ልሰይምሽ
ምኑን ትቼ ማን ልበልሽ
ፍፁም ድንቅ ልጅ ነሽ...
ድንቅ ልጅ ድንቅ ነው ውበትሺ
ከዋክብት ናቸው አይኖችሺ...
አቤት ቅርፀ ስራው የከናፍርሺ...
ፈገግማ ስትይ ሌላ ነው ጥርስሺ..."
"... ማህሙድን ባንተ ነው ምወደው ታውቃለህ አይደል...?” ትከሻውን ተንተርሳ...
"... የሆንክ ሽማግሌ ነገር..."
ዝምታቸው ውስጥ ጠፉ... ማዕበሎቻቸውን ውጠው ዝም...
ትዝታ እና መሃሙድ እዚያ ቦታ አረፍ ብለው ነበር...
|ዘካሪያስ|
°•.•
@yenie_kal •.•°
@yenie_kal ○○○○○○○