የሆንግ ኮንግ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ራሱን ሊያከስም ማቀዱን አስታወቀ
የፓርቲው ሊቀመንበር ሎ ኪንሃይ በሰጡት መግለጫ የሆንግ ኮንግ ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪዎች በአንድ ወቅት የከተማዋ ትልቁ ተቃዋሚ የነበረውን ቡድን ይበተን ወይስ ይቆይ በሚለው ጉዳይ ላይ ድምፅ ለመስጠት እንደሚሰበሰቡ ገልፆል።
2019 የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞና ቻይና በከተማው ውስጥ ያለውን ተቃውሞ ለመቆጣጠር የወሰደችውን እርምጃ ተከትሎ ከተመሰረተ 31 ዓመታት ያስቆጠረው ፓርቲው አሁን ላይ በህይወት ለመቆየት እየታገለ ነው። የቤጂንግ እና የሆንግ ኮንግ መንግስት ግን እንዲህ አይነት እርምጃዎች ለብሄራዊ ደህንነት አስፈላጊ ናቸው ሲሉ ይከራከራሉ።
በ2021 በሆንግ ኮንግ ውስጥ ለኮሚኒስት አገዛዝ ታማኝ የሆኑ ሰዎች እንደ ህግ አውጭ ወይም የአከባቢ ምክር ቤት አባል ሆነው ሊያገለግሉ እንደሚችሉ የሚያረጋግጥ “የአርበኞች ህግ” እየተባለ የሚጠራ ህግ ወጥቷል። ይህ ህግ ደግሞ አንድ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በምርጫ እንዳይሳተፍ በትክክል ይከለክላል።
ሊቀመንበሩ ከፓርቲው ስብሰባ በኋላ ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሚስተር ሎ የፓርቲው አመራሮች “በወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ” ላይ ተመስርተው ፓርቲውን ለማክሰም ወይም ለማቆየት እንዲወስኑ ጥሪ አቅርበዋል። "በሆንግ ኮንግ ዲሞክራሲን ማዳበር ሁሌም አስቸጋሪ ነው፣በተለይም ባለፉት ጥቂት አመታት በጣም ከባድ ሆኗል"ሲሉ ሚስተር ሎ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የፓርቲው አመራሮች ውሳኔ የተደረገው በፖለቲካ ጫና ስለመሆኑ ሲጠየቁ ግን አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
በአሁኑ ሰዓት ፓርቲውን የመዝጋት ሂደት የሚከታተል የስራ ቡድን ተቋቁሟል። በመጪው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከሚሳተፉት አባላቱ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት እርምጃው ከመጠናቀቁ በፊት ማጽደቅ አለባቸውም ተብሏል።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል