ኢትኮፍ ያስገነባውን የቡና ማዕከል አስመረቀ
ኢትኮፍ ያስገነባውን ባለ አምስት ወለል የቡና ማዕከል በትናንት እለት የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት አካላትና እንግዶች በተገኙበት የምርቃት ስነስርእት ተካሂዷል::
ይህ የቡና ማዕከል በውስጡ የመዝናኛ ማዕከልን የያዘ ሲሆን የቡና ቅምሻ ስርዓትን፣ የባህላዊ ቡና አቅርቦትን፣ ሰርቶ ማሳያ፣ የቡና ትርኢት፣ የአርት ጋለሪና ቢዝነስ ሴንተርን ማካተቱም ተገልጿል::
ኢትኮፍ ለመጠጣት የተዘጋጁ የቡና ምርቶችን በራሱ ፋብሪካ ውስጥ እያመረተ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን እነዚህን ምርቶችንም ሃገር ውስጥ ለሚገኘው የውጪ ማህበረሰብ፣ ለኤምባሲዎች፣ ለዲፕሎማቶች፣ ለተለያዩ አየር መንገዶች፣ ደረጃቸውን ለጠበቁ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ያቀርባል፡፡
በተጨማሪም ከሃገር ውጪም ኤክስፖርት የሚያደርግ ሲሆን ለተለያዩ የግል ተቋማት፣ ለመንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች እስከ ቡና ማፍያ ማሽን እንደሚያቀርብ ተነግሯል፡፡
ኢትኮፍ ቡናን ከተለመደው በጥሬና ቆልቶ ወደውጪ በመላክ በርካሽ የሚሸጥበትን ልማድ በመቀየር አዲስ አሰራርን ይዞ የመጣና ለሃገራችን በተለይም ለከተማችን ቱሪዝም ዕድገት የበኩሉን ድርሻ የሚያበረክት ነው ተብሏል::
በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል