ዜና: ከአምስት ሺህ በላይ #የትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች ስልጠና ወስደው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቁ ተደርገዋል ሲል ኮሚሽኑ አስታወቀ
በትግራይ ክልል 5 ሺህ 728 የቀድሞ ታጣቂዎች በተሀድሶ ስልጠና አልፈው ማህበረሰቡን መቀላቀላቸውን የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን አስታወቀ።
የትግራይ የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የመስፈታት እና ወደ ተሓድሶ ስልጠና ማዕከላት የማስገባት ስራ ከአንድ ወር በፊት ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል።
በነዚህ ግዜያት 5 ሺ 728 የቀድሞ ታጣቂዎች በመቀሌና ዕዳጋ ሀሙስ ማዕከላት በማስገባት የተሀድሶ ስልጠናቸውን አጠናቀው ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉን በኮሚሽኑ የፕሮግራም ዕቅድና ክትትል ዳይሬክተር ኮሎኔል በላይ አበበ አስታውቋል።
የቀድሞ ታጣቂዎችን በተሀድሶ ስልጠና የማሳለፍ ሂደት መቀጠሉን ገልጸው አሁን ላይም በመቀሌና ዕዳጋ-ሀሙስ ማዕከላት 889 የቀድሞ ታጣቂዎች ስልጠናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
በቀጣይም በትግራይ ክልል በዓድዋ ከተማ አካባቢ የሚገኘውን የአዲበራህ የስልጠና ማዕከል የዕድሳት ስራ ከ15 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ የተሀድሶ ስልጠና የቅበላ አቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል 75 ሺህ የቀድሞ ታጣቂዎችን በአራት ወራት ውስጥ በተሀድሶ ስልጠና ወደ ማኅበረሰቡ የመመለስ ስራ በተቀመጠው መርሃ ግብር እየተከናወነ ነው ሲሉ ሃላፊው መናገራቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@zena_ethiopia24