ዩኒቨርስቲዎች ውጤታማ ካልሆኑ ህልውናቸው ሊቀጥል አይችልም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ አስጠነቀቁ❗️
ትምህርት ሚኒስቴር #ለዩኒቨርሲቲዎች በጀት የምመድበው በተማሪዎቻቸው እና በመምህራን ብዛት ሳይሆን ባስመዘገቡት ውጤት ልክ ነው ሲል ገለጸ፤ ዩኒቨርሰሲቲዎች ውጤታማ ካልሆኑ ህልውናቸው ሊቀጥል አይችልም ብሏል።
ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር ይቀራል ሲሉ የገለጹት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎቹ ውጤታማ ካልሆኑ ወደ ቴክኒክ ማሰልጠኛነት የሚቀየሩበት ኹኔታ ይኖራል ሲሉ አሳስበዋል።
ትምህርት ሚኒስቴሩ 47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ውጤትን ማዕከል ያደረገ የአፈፃፀም ኮንትራት ስምምነት ትናንት ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራርሟል።
ሥራዎቻቸውም በዚሁ ኮንትራት መሰረት እንደሚለካ የገለጹት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደፊት ለዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው በጀት፣ የሥራ አፈፃፀማቸውን መሰረት ያደረገ እንደሚሆን አስታውቀዋል።
በተለይም ብቃት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራትና ፋይዳቸው የጎላ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን ለማውጣት ጥራት ላይ መስራት ግዴታ መሆኑ በስምምነቱ ተካቷል ብለዋል።
ስምምነቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትክክለኛ መንገድ የሚሰሩና ተጠያቂነት ያለባቸው እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃትና በጥራት እንዲፈፅሙ በተለይም ሙስናን ማጥፋት ግዴታ መሆኑንም አንስተዋል።
@zena_ethiopia24