ዜና central


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


አዳዲስ መረጃዎችን እና ታሪኮችን ከኢትዮጵያ እናደርሳችኋለን።

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Simba
#ጉምሩክ🚨

" አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች አስወጡ !! " - ጉምሩክ

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፦

" መንግስት ያወጣውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የብሔራዊ ባንክ ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ መደረጉ ይታወሳል።

በመሆኑንም ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ሰነዱ ተቀባይነት ባገኘበት እለት በነበረው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ  ይደረጋል።

ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ/ም በኋለ ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ደግሞ በአዲሱ የውጭ የምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ  መሰረት በየእለቱ በሚኖረው የምንዛሬ ተመን ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ ይደረጋል።

የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ባለመገንዘብ የተነሳ እቃዎችን በደረቅ ወደብ ያከማቹ አስመጭዎች አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች ሊያስወጡ ይገባል።

የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በመተላለፍ እቃዎችን በደረቅ ወደቦች ያላግባብ በማከማቸት በገበያ ላይ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን። "




የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓት) ጠቅላላ ጉባዔውን ሊያደርግ መሆኑን በመገናኛ ብዙኃን መነገሩን ተከትሎ ቦርዱ ለፓርቲው የጻፈው ደብዳቤ ከታች ተያይዟል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላን በስልክ ምን አሉት?


Репост из: Simba
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ለኔዘርላንድ ምትሮጠው አትሌት ሲፋን ሀሰን በማራቶን ውድድር 1ኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያውን ከመውሰዷም ባለፈ የገባችበት ሰዓት 2:22:55 የኦሎምፒክ ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል።

በሀገራችን ልጅ ቲኪ ገላና ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ነው የሰበረችው።

አትሌቷ በዚሁ በፓሪስ ኦሎምፒክ በ5 ሺህ ሜትር እና በ10 ሺህ ሜትር ውድድር ተወዳድራ ሁለቱንም ሶስተኛ በመውጣት 2 የነሃስ ሜዳሊያ አግኝታለች።

የዛሬው የ42 ኪሎ ሜትር የማራቶን ወርቅ ሜዳሊያዋ በፓሪስ ኦሎምፒክ 3ኛዋ ነው።

የአትሌቷ ብቃት እና ጥንካሬ በርካቶችን አስገርሟል።


የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለህወሓት የሰጠውን በልዩ ሁኔታ የመመዝገብና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ውሳኔ አስመልክቶ ከህወሓት የተሰጠ መግለጫ‼️


በኢትዮጵያ ባንኮች መካከል አዲስ አዝማሚያ እየታየ ነው። የመግዛትና የመሸጫ ክፍተቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ክፍተቶቹ በዚህ ሳምንት ወደ 15 ብር ከፍ ብሏል።

ለጥቁር ገበያ መመስረት ዋናው ምክንያት ይህ ነው። ለምንድነው አንድ ሻጭ ዶላራቸውን ለባንክ በገበያ ዋጋ ይሸጣል ስለዚህ ባንኮች ከትርፍ ይልቅ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮቹ በባንኮች የሚቆጣጠረው ጥቁር ገበያ እንዳያቋቁሙት ሊንቀሳቀስ ይገባል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
"ፈጣሪ ዛሬ ሰምቶናል" - ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ


በማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ምክንት ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል  ነባራዊ ሁኔታ የለም-  የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ምክንት ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል  ነባራዊ ሁኔታ የለም ሲል  የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የአገልግሎቱ ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር)ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት በበጋ ስንዴ ልማት 107 ሚሊየን ኩንታል መሰብሰቡንና  በሌማት ትሩፋትና በአረንጓዴ ዐሻራም አመርቂ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጣዊ እና ውጫዊ  ተግዳሮቶችን በመቋቋም  ቀጣይነት ያለው እድገት በማስመዝገብ  አይበገሬነቱን ማስመስከሩን ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም ኢትዮጵያ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መግባቷን አንስተው ጠቀሜታውን አብራርተዋል፡፡
በአጠቃላይ ማሻሻያው ቀጣይነት ያለውና ሁሉን አቀፍ እድገትን ለማበረታታት እንዲሁም የታለመውን ፋይናንሻል መረጋጋት ግልፅነትን ለማሳደግ፤ የልማት ፕሮጀክት ውጤታማነትን እንዲሁም የመንግስትን ገቢን ለማሻሻል ያለመ ነው ብለዋል፡፡
በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዙሪያ ያሉ ቭዥታዎችን ለማጥራት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በተለያዩ  ምሑራን በተለያዩ አማራጮች ማብራሪያ መሰጠቱንም አንስተዋል፡፡
በዚህም ማሻሻያው በታቀደለትና በተቀመጠለት አቅጣጫ መሰረት በውጤታማነት እየተተገበረ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
አብዛኛው የንግዱ ማህበረሰብ የማሻሻያውን አስፈላጊነት በመረዳት በሚያስመሰግን አኳኋን የንግድ እንቅስቃሴውን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል  ግን ተገቢ ያልሆኑ አዝማሚያወዎች እየታዩ ነው ያሉት ለገሰ(ዶ/ር) ህገ ወጥነትንና የራስን ስግብግብ ፍላጎትን በሌላው ላይ በመጫን ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ምርትን ለመደበቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ መኖሩን ገልፀዋል፡፡
ይህ ድርጊት ምክንያታዊ መሰረት የሌለውና ተቀባይነት የለውም  ድርጊትነው ፤በዚህም  መንግስት የጀመረውን የቁጥጥር ስራ በማጠናከር የህግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ይሰራል ነው ያሉት፡፡
አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታም በማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ምክንያት ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል  ነባራዊ ሁኔታ እንደሌለም አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም መንግስት በዓመቱ ህግና ስርዓትን ለማረጋገጥና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ሰፋፊ ስራዎች ማከናወኑን ገልጸዋል።
 
ነፍጥ ያነገቡ ሃይሎች ወደ ውይይት እንዲመጡ ሁሉንም የሰላም በሮች ክፍት አድርጎ ጥሪ ማድረጉንና ድርድሮችንም ማድረጉን ተናግረዋል።
 
በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸው፥ በዚህም ከምርት ተስተጓጉለው የነበሩ አካባቢዎች ወደመደበኛ ህይወት መመለሳቸውን ገልጸዋል።
 
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከነሃሴ 29  እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2016ዓ.ም የመጀመሪያውን አፍሪካ ከተሞች ፎረም  እንደምታስተናግድና  በርካታ ሁነቶች እንደሚካሄዱ ተናግረዋል፡፡
 
የመክፈቻ ዝግጅቱም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚካሄድ  ነው የተናገሩት፡፡
 
ፎረሙ ስኬታማ እንዲሆን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመስገን ጥሩነህ የሚመራ ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡


📈 Binance USD Prices

🕒 Time: 01:22 PM

1. 124.10 ETB
2. 124.20 ETB
3. 124.21 ETB
4. 124.27 ETB
5. 124.30 ETB
6. 124.35 ETB
7. 124.37 ETB
8. 124.39 ETB


ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፦በቅርቡ የተሰጠ የህወሓት ምዝገባ በማስመልከት ያለን ቅሬታ ማቅረብን ይመለከታል

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 03 ቀን 2016ዓ.ም ለህወሓት በልዩ ሁኔታ የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን ይታወቃል።

ቦርዱ ይህንን በማስመልከት በተመሳሳይ ቀን በሰጠው መግለጫ በተራ ቁጥር 2 ደግሞ ህወሓት የፓርትው ኃላፊዎች ስምና ፊርማ የያዘ ሰነድ ማቅረቡን ይፋ አድርጓል።ይሁንና ይህ የምዝገባ ጥያቄ ህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀው እና እኛ ደግሞ ለዚሁ ምዝገባ ብለን የፈረምነው ምንም ዓይነት ሰነድ ሳይኖር ግለሰዎች ብቡድን ተደራጅተው ከድርጅቱ አሰራር ውጭ የፈፀሙት ያልተገባ ተግባር መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።

በመሆኑም ይህ ድርጊት እኛ የማናውቀው መሆኑን እየገለፅን በድርጅቱ ስም ምዝገባ የጠየቁ ግለሰዎችም እኛን ሳያስፈቅዱ የፈፀሙት መሆኑን እየገለፅን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለነዝህ ግለሰዎች የሰጠው ምዝገባ በተጭበረበረ ማስረጃ መሰረት የተሰጠ በመሆኑ መልሶ እንዲመረምረው እንጠይቃለን።

የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝር እና ፊርማ ቀጥለን የምናቀርብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

ጌታቸው ረዳ


TSEDEY BANK just updated their rates📈

🏦 TSEDEY BANK
📅 Rate Date: 10 Aug 2024

Currency Buying Selling
-------- ------ -------
🇺🇸 USD 105.9084 116.4992
🇪🇺 EUR 115.5673 127.124
🇬🇧 GBP 128.6098 141.4708
🇦🇪 AED 25.8096 28.3905


DASHEN BANK just updated their rates📈

🏦 DASHEN BANK
📅 Rate Date: 10 Aug 2024

Currency Buying Selling
-------- ------ -------
🇺🇸 USD 103.7889 115.2057
🇪🇺 EUR 112.5384 124.9176
🇬🇧 GBP 127.5952 141.6307
🇦🇪 AED 25.5721 28.3851
🇨🇦 CAD 67.8777 75.3442
🇨🇳 CNY 13.0105 14.4416
🇸🇦 SAR 25.037 27.7911


BANK OF ABYSSINIA just updated their rates📈

🏦 BANK OF ABYSSINIA
📅 Rate Date: 10 Aug 2024

Currency Buying Selling
-------- ------ -------
🇺🇸 USD 103.0102 115.3714
🇪🇺 EUR 112.5283 126.0317
🇬🇧 GBP 125.3418 140.3828
🇦🇪 AED 25.1019 28.1141
🇨🇦 CAD 67.2067 75.2715
🇨🇭 CHF 113.2803 126.874
🇨🇳 CNY 12.8601 14.4033
🇳🇴 NOK 8.5226 9.5454
🇸🇦 SAR 24.5707 27.5192
🇸🇪 SEK 8.7856 9.8399


AWASH BANK just updated their rates📈

🏦 AWASH BANK
📅 Rate Date: 10 Aug 2024

Currency Buying Selling
-------- ------ -------
🇺🇸 USD 102.7621 114.3741
🇪🇺 EUR 111.4249 124.0159
🇬🇧 GBP 132.2855 147.2337
🇦🇪 AED 27.9771 31.1384
🇨🇦 CAD 74.2608 82.6523
🇨🇭 CHF 116.9876 130.2072
🇸🇦 SAR 27.3916 30.4868


COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA just updated their rates📈

🏦 COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
📅 Rate Date: 10 Aug 2024

Currency Buying Selling
-------- ------ -------
🇺🇸 USD 101.8041 111.9845
🇪🇺 EUR 111.1701 122.2871
🇬🇧 GBP 123.781 136.159
🇦🇪 AED 27.7199 30.4919
🇦🇺 AUD 61.6789 67.8468
🇨🇦 CAD 68.3498 75.1848
🇨🇭 CHF 112.1727 123.39
🇨🇳 CNY 13.0967 14.4064
🇩🇰 DKK 13.735 15.1085
🇯🇵 JPY 0.6397 0.7037
🇰🇼 KWD 316.9232 348.6155
🇳🇴 NOK 8.6781 9.546
🇸🇦 SAR 27.1239 29.8363
🇸🇪 SEK 8.9226 9.8149


OROMIA BANK just updated their rates📈

🏦 OROMIA BANK
📅 Rate Date: 10 Aug 2024

Currency Buying Selling
-------- ------ -------
🇺🇸 USD 103.9831 117.5009
🇪🇺 EUR 113.4144 128.1583
🇬🇧 GBP 132.4849 149.7079
🇦🇪 AED 28.3086 31.9887
🇨🇭 CHF 120.0175 135.6198
🇸🇦 SAR 27.7066 31.3085


NIB INTERNATIONAL BANK just updated their rates📈

🏦 NIB INTERNATIONAL BANK
📅 Rate Date: 10 Aug 2024

Currency Buying Selling
-------- ------ -------
🇺🇸 USD 104.1287 116.6242
🇪🇺 EUR 113.6405 127.2773
🇬🇧 GBP 132.6819 148.6037
🇦🇪 AED 28.349 31.7509
🇨🇦 CAD 75.7686 84.8608
🇨🇭 CHF 120.2827 134.7166
🇸🇦 SAR 27.7462 31.0758


የኢዜማ ዋና ጸኃፊ አበበ አካሉ ከፓርቲው በገዛ ፍቃደቸው ለቀቁ፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ከምስረታው ጀምሮ በዋና ጸኃፊነት ሲሰሩ የቆዩት አበበ አካሉ ከሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከፓርቲው መልቀቃቸውን ለምርጫ ቦርድ ከፃፉት ይፋዊ ደብዳቤ አሻም ለመረዳት ችላለች፡፡

ዋና ጸኃፊው መልቀቃቸውን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹ ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስብስብ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የዜግነት ፖለቲካን በማቀንቀን፣ አቅምና ችሎታዬ በፈቀደልኝ መጠን የበኩሌን አስተዋጽኦ ለሰላማዊ ትግሉ ሳበረክቴ መቆየቴ እሙን ነው ›› ሲሉ ያለፉት ዓመታት የፖለቲካ ተሳትፏቸውን አስታውሰዋል፡፡

ይሁንና ‹‹ እያደረ በሚስተዋለው የፓርቲው አቋምና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ውስጥ በኃላፊነትም ሆነ በአባልነት መቀጠል ስለማልፈልግ፣ ከሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ›› በይፋ መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

https://t.me/zenacentral


የኢትዮጵያ መንግስት ብር ለመንሳፈፍ የወሰነው በጦርነት፣ በድርቅ እና በዋጋ ንረት ተባብሶ ለዓመታት የዘለቀው የኢኮኖሚ ችግር ነው። የመጀመሪያ ድንጋጤ ቢኖርም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር በመዋቅራዊ ማሻሻያ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ተስፋ አድርጓል። የማህበራዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብሮች እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህዝብ አገልግሎት ሰራተኞች የደመወዝ ድጎማዎች ተጽእኖውን ለመቅረፍ እንደ ሰፊው ስትራቴጂ አካል ቃል ገብተዋል. በዚህ ግርግር ወቅት ህዝቡ ተረጋግቶ ምክንያታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ተጨማሪ

ምንጭ፡ addisfortune
https://t.me/zenacentral

Показано 20 последних публикаций.