🗓ምልክቴ ነሽ
ምልክቴ ነሽ ድንግል ለሕይወቴ
ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ
ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ
ፀጋሽ ጎብኝቶኝ ቃል ኪዳንሽ
ተስፋ ያረኩት አልተበተነም
እንባዬም መሬት ከቶ አልወደቀም
ለበጎ ሆነ ማልቀስ ማንባቴ
ሰላም ሰፈነ በእልፍኝ በቤቴ
ቅኔ ነጠቅሁኝ የአባ ጊዮርጊስን
ቆምኩኝ ቅዳሴ የሕርያቆስን
የያሬድ ዜማ ሞላ በልቤ
የለም ወጀቡም ቀርባኝ መርከቤ
ወገቤን ታጠቅሁ ጭንቀቴን ጥዬ
ዛሬስ በደስታ ይፍሰስ እንባዬ
የሐዘን ልብሴን ድንግል ቀይራ
የደበዘዘው ህይወቴ በራ
የአራራይ ዜማ ዛሬ ተማርኩኝ
ፍቅሯ አሸነፍኝ እጀን ሰጠሁኝ
ቅኔ በልቤ ተመላለሰ
የድንግል ክብር ውስጤ ነገሰ
የዘረጋሁት እጄ ተሞላ
ማርያም ሆናልኝ ጥላ ከለላ
የውስጤ ፀሎት ዛሬ ሌላ ነው
የድንግል ክብር ምልጃ ቀየረው
ዛሬ ጎጆዬ አንፀባረቀች
ያማረ ሰንፔር ዕንቁ መሰለች
ክንዴ ከፍ ከፍ አለልኝና
ሰዋሁ ለድንግል ይህን ምስጋና
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️
✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨
ምልክቴ ነሽ ድንግል ለሕይወቴ
ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ
ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ
ፀጋሽ ጎብኝቶኝ ቃል ኪዳንሽ
አዝ
ተስፋ ያረኩት አልተበተነም
እንባዬም መሬት ከቶ አልወደቀም
ለበጎ ሆነ ማልቀስ ማንባቴ
ሰላም ሰፈነ በእልፍኝ በቤቴ
ቅኔ ነጠቅሁኝ የአባ ጊዮርጊስን
ቆምኩኝ ቅዳሴ የሕርያቆስን
የያሬድ ዜማ ሞላ በልቤ
የለም ወጀቡም ቀርባኝ መርከቤ
አዝ
ወገቤን ታጠቅሁ ጭንቀቴን ጥዬ
ዛሬስ በደስታ ይፍሰስ እንባዬ
የሐዘን ልብሴን ድንግል ቀይራ
የደበዘዘው ህይወቴ በራ
የአራራይ ዜማ ዛሬ ተማርኩኝ
ፍቅሯ አሸነፍኝ እጀን ሰጠሁኝ
ቅኔ በልቤ ተመላለሰ
የድንግል ክብር ውስጤ ነገሰ
አዝ
የዘረጋሁት እጄ ተሞላ
ማርያም ሆናልኝ ጥላ ከለላ
የውስጤ ፀሎት ዛሬ ሌላ ነው
የድንግል ክብር ምልጃ ቀየረው
ዛሬ ጎጆዬ አንፀባረቀች
ያማረ ሰንፔር ዕንቁ መሰለች
ክንዴ ከፍ ከፍ አለልኝና
ሰዋሁ ለድንግል ይህን ምስጋና
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️
✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨