♥️ባለታክሲው 🚐💝
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በከምርጦችማህደር የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ
ክፍል 1
ባለታሪኳ ሊዲያ ሀጎስ
ከታሪኬ ባትማሩ እንኳን ሀሳብ አስተያየታችሁ እኔን ስለሚጠቅመኝ አንብቡትና ሀሳባችሁንን አካፍሉኝ
ሊዲያ ሀጎስ እባላለሁ ተወልጄ
ያደኩት እዚሁ አዲስ አበባ
በተለምዶ አለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ነው።
እንዳብዛኛው ኢትዮጵያዊ መካከለኛ
ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች ነው የተወለድኩት ታድያ የዛሬው ታሪኬ የሚጀምረው የ10ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነበር።
የምማረው አየርጤና ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ነበር (ምናልባት እዛ አከባቢ የሆናችሁ ታውቁታላችሁ) እናም ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድም
ለመመለስም ግዴታ ታክሲ መጠቀም አለብኝ ምክንያቱም ት/ቤቱ ከሰፈሬ በጣም ይርቃል ከዛ እንደልማዴ ትምህርት ጨርሼ ወደ ሰፈሬ የሚሄድ ታክሲ እየጠበኩኝ እያለ አንድ ላዳ ታክሲ መቶ አጠገቤ ቆመና ሹፌሩ በመስኮት በኩል ተንጠራርቶ አለምባንክ ነሽ አይደል ነይ ግቢ አለኝ እኔም ትንሽ
ተናድጄ አመሰግናለሁ እኔ ታክሲ ነው የምጠብቀው ለላዳ የሚሆን ሳንቲም የለኝም አልኩት አውቃለው
ባክሽ ነይ ግቢ እኔም ወደዛው ስለሆንኩ እግረ መንገዴን ላድርስሽ ብዬ ነው ምንም አላስከፍልሽም አለኝ
አልገባም አልኩት ከመኪናው ወርዶ ወደኔ መጣ በጣም ቆንጆ ነው እዚ ከምትቆሚ ብትገቢ ይሻልሻል ታክሲ
አታገኚም አለኝ የገቢናውን በር ከፍቶ በእጁ ወደውስጥ እያመለከተኝ እውነትም ረጅም ሰዓት ቆሜያለሁ በዛ ላይ እርቦኝ ነበር ገባሁ መንገድ ጀመርን ግን ሰፈሬ አለምባንክ መሆኑን እንዴት አወክ? አልኩት
ምን እዚ ታክሲ ተራ አይደል እንዴ እንደ አደባባይ ሀውልት ቆመሽ ምትውይው አለኝ ከት ብዬ ሳኩኝ
ለረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቅ ሰው እያወራን ሰፈር ደረስን ልወርድ ስል ግሩም እባላለሁ ስልኬ እዚ ላይ አለልሽ በማንኛውም ሰዓት ብትደውይ እገኛለሁ አለኝ ቢዝነስ ካርዱን እየሰጠኝ አመስግኜው ወደ ቤት ገባሁ ግን በጣም ደስ ደስ እያለኝ ነበር ሁሉ ነገሩ ጨዋታው ቀልዱ ውበቱ ያቺን ትንሽ ልቤን አሸበራት።
እሱን እያሰብኩ ነጋ ጠዋት ላይ እንደልማዴ ወደ ትምህርት ለመሄድ ዩኒፎርሜን ለብሼ ቦርሳዬን አንግቼ እየተጣደፍኩ ከቤት ስወጣ ልክ የግቢ በራችን መውጫ ላይ ግሩም ላዳ
ታክሲውን ተደግፎ ቆሟል።
እሱ መሆኑን ሳአለቀቀኝም ነበር የደነገጥኩት ምን ትሰራለህ እዚ አልኩት መጀመርያ እንዴት አደርክ አይቀድምም? አለኝ ረጋ ብሎ
እሱማ ደና ብታድር አይደል እንዴ ያገኘሁክ ይልቅ ምን ትሰራለህ?ድንጋጤዬ አለቀቀኝም
አረ ተረጋጊ ሴትዮ ባልሽ ቤት የመጣሁ አስመሰልሽው እኮ እኔ እዚ የታመመ ሰው አምጥቼ በዛው በበራቹ በኩል
ሳልፍ ትዝ ብለሽኝ ቆይ እስኪ እቺ ልጅ ደሞ እንዳመሏ ታክሲ አታ እንዳትንገላታ ብዬ እየጠበኩሽ ነበር አለኝ
እየሳቀ ቤታችንን እንዴት አወቅከው? አፈጠጥኩበት እንኳን ቤታቹን የትምህርት ቤት ክፍልሽን ሁሉ
አውቀዋለሁ አረ እንደውም የምትቀመጪበትንም ቦታ
አውቀዋለሁ ይልቅ ነይ ግቢ ትምርት እንዳይረፍድብሽ አለኝ የገቢናውን በር እየከፈተ አሁን የባሰ ግራ ተጋባሁ
እኔ በህይወቴ ለመጀመርያ ጊዜ ትናንትና ነው ያየሁት እሱ እንዴት ስለኔ ይሄን ያህል ሊያውቅ ቻለ?
ይሄን እያሰብኩኝ ተከፍቶ ወደሚጠብቀኝ በር ገባሁ........
ክፍል ሁለት ከ250 Like 👍በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ።
ሼር