♥️ባለታክሲው🚕
💝ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ
ክፍል 4️⃣
ስልኩ ላይ ደወልኩ ይጠራል አይነሳም ድጋሜ ሞከርኩ ከብዙ ጥሪ በኃላ
አነሳው ድምፁ ይንቀጠቀጣል ሄሎ ማማዬ አለኝ ግሩሜ ምን ሆነህ ነው
የተፈጠረ ችግር አለ ? አልኩት በጣም ደንግጬ ማማዬ ሰው ገጨው እዚ
ቃሊቲ አከባቢ ሰዎቹን አድርሼ ስመለስ የሆነች ልጅ ገጨሁ አለኝ ከአልጋዬ ዘልዬ
ተነሳሁ ግሩሜ ተ ተረፈች ልጅቷ ተረፈች ? የማወራው ሁሉ ጠፋብኝ አላውቅም
በጣም ተጎድታለች ።
፣
እራሷን አታውቅም አሁን ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ነን ድንገተኛ ክፍል
አስገብተዋታል ። ተረጋጋ የኔ ጌታ እኔ አሁን ኮንትራት ታክሲ ፈልጌ እመጣለሁ
ብዬው ስልኩን ዘግቼ እናቴን ቀሰቀስኳት (እናቴ እኔ ከወለድኩ ጀምሮ እኛ ቤት
ነው የምታድረው) የሆነውን ነገርኳትና ልጄጋ አስተኝቻት ወጣሁ አንድ የማውቀው
ሹፌር የግሩሜ ጓደኛጋር ደውዬለት እሱ መቶ ወሰደኝ ደረስን እውነትም ልጅቷን
ስትነቃ ካልሆነ ገብተን ማየት እንደማንችል ነገሩን እዛው አደርን ።
፣
እንዴት ሊገጫት እንደቻለ ጠየኩት ልጅቷ የሆቴል ሴት ነች ለስራ ወጥታ
አስፋልት ዳር የቆሙ መኪኖች ስር ቆማ ነበር እሱ ደግሞ መኪኖች ስለከለሉት
አላያትም ብቻ ሰዓትም ስለሄደ ቶሎ ወደቤት ለመድረስ ቸኩሎ በፍጥነት
እያሽከረከረ እሷ ለመሻገር ስትሞክር አደጋው ደረሰ ደግሞ ዜብራ ላይ መሆኑ
የበለጠ እሱን ጥፋተኛ ያስብለዋል ። የከፋ እስርም እንደሚጠብቀው የታወቀ
ነው ።
፣
ጠዋት ላይ ጓደኞቹም ሰምተው መጡ አንደኛው ጓደኛው ልጅቷ ከተስማማች
ነገሩ ፖሊስጋር ሳይደርስ አስፈላጊውን ሁሉ አድርገን ድና እስክትነሳ
ልናስታምማት እንደምንችል ነገረን ልጅቷም ነቅታ ስለነበር ገብተን አየናት እግሯ
በጣም ተጎድቷል ። የሆነውን ነገርናት እኔ በተለይ በእምባ እየታጠብኩ ግሩሜን
እንዳትከሰው ለመንኳት እሷም እኔ ወጪዬን ሸፍናቹ ካሳከማቹኝ ምን መክሰስ
አስኬደኝ አለችና ተስማማች ።
፣
ከዛም እዛ እየተመላለስን ማስታመም ጀመርን ግሩሜ ስራ ሲሄድ እኔ
እያስታመምኳት እሱ ሲመለስ እያስታመማት ከ2 ሳምንት የሆስፒታል ቆይታ በኃላ
መውጣት እንደምትችል ዶክተሮቹ ነገሩን ሆኖም ከሀኪምቤት ብትወጣም ወደ
ሙሉ ጤንነቷ ለመመለስ ቢያንስ ለሁለት ወር ቤት ውስጥ ተኝታ ብዙም
እንቅስቃሴ ሳታደርግ መቆየት እንዳለባት ነገሩን ያው ልጅቷ የድሬደዋ ልጅ ናት
የምታውቀው ዘመድም ሆነ ጓደኛ የላትም ሆቴል ነበር የምትሰራው ስለዚህ
አማራጩ እኛ ቤት አድርጎ ማስታመም ነው ደግሞም ግዴታችንም ነበር ይዘናት
ወደቤት ገባን ።
፣
ከዚ በኃላ ኑሮ ከባድ እየሆነብን መጣ በአንድ የታክሲ ሹፌር ደሞዝ የቤት ኪራይ
ተከፍሎ የልጃችን ወጪ የታማሚዋ ሲጨመር በጣም እየከበደን መጣ ባንክ
የነበረችን ገንዘብም ለልጅቷ ህክምና ወጥቶ አለቀ ስለዚህ እኔ በተመረቅኩበት
የፀጉር ሞያ ስራ ማፈላለግ እንዳለብኝ ወሰንኩ እናቴም ልጄን እንደምትይዝልኝ
ነገረችኝ ግሩሜ የ3 ወር ልጃችንን ጥዬ መዋሉ ደስ ባይለውም ተስማማና ፒያሳ
አከባቢ ፀጉር ቤት በጥሩ ደሞዝ ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩ ።
፣
ጠዋት ተነስቼ ለታማሚዋ ቁርስና ምሳ ሰርቼ አጠገቧ አድርጌላት ልጄን ለናቴ
አቀብዬ ወደ ስራዬ ሄዳለሁ ህይወት ከባድ ቢሆንም ግን ለፍቅር ሁሉም ዋጋ
ያንሰዋልና እኔና ግሩሜ እኩል እየደከምን ማታ መግባት ጀመርን በዚህ መልኩ
እኔም ስራዬን እየለመድኩት ታማሚዋም ከህመሟ እየዳነች ጊቢ ውስጥ
መንቀሳቀስ አንዳንዴም ሰፈር ውስጥ ግሩሜ ደግፏት እየወጣች መራመድ
ጀመረች ልጄም በእናቴ እንክብካቤ እያደገችልኝ መጣች ። ግን ሁሉም በዚህ
መልኩ አልቀጠለም ነበር ያላሰብኩት ነገር ተፈጠረ ።
፣
አንድ ቀን እንደልማዴ የቤት ውስጥ ስራዬ ጨራርሼ ወደ ስራ ሄድኩ ከቀኑ 8
ሰዓት ሆኗል መብራት ከጠፋ 2 ሰዓት አለፈው ያለስራ መቀመጣችንን ያየችው
የፀጉርቤቷ ባለቤት ሊዲያ ወደቤት ሂጂ በቃ እዚ ከምትቀመጪ ስራ ካለሽ ሰራሪ
ነገ ጠዋት ነይ አለችኝ በጣም ደስ አለኝ እቤት ብዙ ስራ ይጠብቀኝ ነበር እሺ
ብዬ ወደቤት ተመለስኩ እቤት ስደርስ ተከራይ ሁሉ ስራ ስለሚውል ጊቢው ጭር
እንዳለ ነው ።
፣
የቤቱ በር ገርበብ ብሏል ምናልባት ታማሚዋ ተኝታ ከሆነ እንዳቀሰቅትሳ ብዬ
ኮቴዬን አጥፍቼ ወደ ውስጥ ገባሁ እሷ ከምትተኛትበ ክፍል ያልተለመደ አይነት
የማቃሰት ድምፅ ሰማሁ እግሯን አሟት ይሆን ብዬ እየተጣደፍኩ ወደክፍሉ
አመራሁና ገርበብ ያለውን በር ከፍቼ ገባሁ አይኔ ያየውን ማመን አልቻለም
በምቆኩበት ሀውልት ሆኜ ቀረሁ ።
ክፍል አምስት ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍ማድረግ አይርሱ‼️