አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE
ስለ ጥበብ በጥበብ እናወራለን ከኛ ጋራ ሁኑ!
ግጥም፣ ወግና መጣጥፍ፤
ታሪክና ታሪካዊ ንግሮች፤
ምርጥ ምርጥ እባባልና ምስሎች፤
ሰበርና ወሳኝ መረጃዎች፤
የድምጸ መልካሞች ሙዚቃ፤
.
.
በሥነ-ኪን አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!
.
.
.
.
አትራኮሰ-ጥበብ!!!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


፵፯ ኛው የካራማራ ድል።

መልካም በዓል!

አትራኮሰ-ጥበብ!


ትንቢተ ኢሳያስ (ባቢ) የጋሽ ጥላሁን ገሰሰን "ቆሜ ልመርቅሽ" ደግሞ እንዳቀነቀነው።
🎤🎤🎤

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧


ካራማራ የዘመናችን አድዋ!

#ኢትዮጵያ #ካራማራ | ጀግናዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት የሱማሊያ ወራሪ ጦርን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ የካራማራን ድል ላስመዘገበበት የድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ!

ታላቅ ክብር ይህንን ድል ላስመዘገበው ጀግናዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት ይሁን!!


ትንቢተ ኢሳያስ የደረጄ ዱባለ "ሀገሬ" ሙዚቃን ደግሞ እንዳቀነቀነው።

🎤🎤🎤

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧


"አዝማሪሽ እኔ ነኝ"
ከነ ሙሉ ቅንብሩ!

ድምጻውያን
ትንቢተ ኢሳያስ (ባቢ)
ዮሴፍ በቀለ
ያሬድ ጥበቡ
ዳዊት በቀለ

ግጥም
ብሩክ ሚፍታ (አትራኮስ)

ዜማ
ዳዊት በቀለ

መሰንቆ ተጫዋች
ደግሰው አበበ

ድምጽ ቀረጻ፣ ቅንብር፣ ማስተሪንግ
ዳኜ ደጀኔ (ከበሮ ስቱድዮ)

📻📻📻
https://t.me/ATRACOSE
📻📻📻


ዋ! .... ያቺ ዓድዋ

ዋ! ....
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ ....
ባንቺ ብቻ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና ....

ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰዉብሽ ለት፤

ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ

ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሣኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዊ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው-እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው - በለው - በለው - በለው!

ዋ! .... ዓድዋ....
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በጻኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጐራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ' በለው-በለው!

ዋ!.... ዓድዋ ....
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እንደገና።

.... ዋ! .... ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ ....

የካቲት - ፲፱፻፰፬ - ዓድዋ
እሳት ወይ አበባ ከጸጋዬ ገብረ መድኅን

👇👇👇
https://t.me/ATRACOSE
👇👇👇


እንኳን አደረሳችሁ!


ነገ ይጀምራል!

የ1446ኛው የረመዳን ፆም ነገ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገልጿል።

ምክር ቤቱ፣ ጨረቃ ዛሬ በመታየቷ ህዝበ ሙስሊሙ በፆምና ጸሎት የሚያሳልፈው የረመዳን ወር ነገ እንደሚጀመር አስታውቋል።

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የፆም ወር ይሁንላችሁ!


የአምለሰት ሙጬ ፕሮዳክሽን የሆነው ማያ ሚድያ ተዋናይ እንፈልጋለን ብሎ በዩቲዩብ ገጹ ላይ ይህንን ጥሪ አቅርቧል። መስፈርቱን የምታሟሉ እድሉን ተጠቀሙበት!


Репост из: Janderebaw Media
ጾም የሥጋ ምኞትን የምታጠፋ የነፍስን ቁስል የምታደርቅ ለጎልማሶችም ጸጥታንና እርጋታን የምታስተምር ደገኛ ሥርዓት ነች፡፡

እያንዳንዱን ዕለት ከክርስቶስ ጋር ሆኖ ለማሳለፍ ዝግጁ ናችሁ? አብረን እንጓዝ።

ፍሬ የምናፈራበት ጾም ያደርግልን።


ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የአብይ ጾም ወራት!


የአትራኮሰ-ጥበብ መስራችና የበላይ ሀላፊ የሆነው፤ ቡድኑ በሰራቸው ድራማና ፊልም የቴሌቭዥንና የሬድዮ ፕሮግራም ላይ በተለያዩ ሞያዎች ሰርቶ የሚያሰራው ኃይሌ ባልቻ ዛሬ የካቲት ፲፮/፪፼፲፯ ዓ.ም. የተወለደበት ቀን ነው።

አትራኮስ መልካም ልደት ብሎ ይመኝለታል። እስከዛሬ ላደረገው አስተዋጽኦም ምስጋናውን ያቀርባል።

👇👇👇
https://t.me/ATRACOSE
👆👆👆


ዛሬ የካቲት አስራ አምስት የዘመን ፈገግታው ሞገስ፣ ትሁቱ ቤታ በክብር ተሞሸረ። "ይድረስ ለአትራኮሳውያን" ተብለን በመታደም እኛም በአክብሮት ዳርነው!

መልካም የትዳር ዘመን ይሁንልዎ አይተ ቤተሰብ የማነህ!!!

ፎቶ፦ #ብሩክ_ሚፍታ_(አትራኮስ)

👇👇👇
https://t.me/ATRACOSE
👆👆👆





Показано 15 последних публикаций.