Репост из: الشباب السلفيين
ለመላው ሰለፍዮች አድርሱልኝ አደራ!!
--------—----------------------
#አንድ_እንሁን_በሀቅ
▬▬▬▬▬▬▬▬
ግራ ቀኝ እናስብ ይቅር መከፋፈል፡
አይጠቅመንምና የመልስ ምት ወንፈል፡
አንዳችን ለአንዳችን እንኳን ተጠላልተን፡
ወንድም ለወንድሙ እንኳን ተበላልተን፡
ጠላት ይፈልጋል እኛን ለመበተን፡
መታገስ ሲገባን መልስ ተሰጣጥተን፡
እንደ ተራ ነገር ጎራ ተለያይተን፡
ቂለ ወቃል የሚል ተራ ስም አውጥተን፡
ቀጥ ያለውን መስመር በስሜት ረስተን፡
የተውሒዱን ነገር ትተነው ዘንግተን፡
በራሳችን ጊዜ ጠላት አመቻችተን፡
ተንጋለን ቁመናል ለዘብህ አመችተን፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በፀጉር ስንጠቃ ከምንጠራጠር፡
ለቃላት ውርወራ ከምንቀጣጠር፡
ጠላት አንገት ይድፋ አንድነት እንፍጠር፡
የሱና ጠበቃ የሆንከው ወንድሜ፡
ስጋህ ከስጋዬ ደምህም ከደሜ፡
በመንሀጀ ሰለፍ እጂግ ተዋህዶ፡
በፍቅር አሳልፈን ሙቀትም በረዶ፡
አሁን ምን አገኘን ምን ተሰማ መርዶ፡
ሸይጧን በየት ገባ መሀባውን ንዶ፡
እጂግ ብዙ አመታት በፍቅር ተጋምደን፡
በአሏህ እገዛ ብዙ ስኬት ወልደን፡
ብዙ ጠላቶችን አፈራርሰን ንደን፡
በርካታ ጥመቶች ታግለን አስወግደን፡
አሁን ምን ተገኘ ምን መጣብን በኛ፡
ማን ተመለከተን ምን አይነት ቀበኛ፡
እንደት አይነት ቡዳ ምን መስሎ ገባብን፡
በፍቅር መካከል ጥላቻ ዘራብን፡
ጨነቀን በአሏህ ምን ማድረግ አለብን!?
እንባዬ ፈሰሰ እኔ በጣም ከፋኝ፡
ከማን ጋ ልሰለፍ ምን ቃል ልበል ጠፋኝ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ማን በምን ከፈተው የፊትናውን ሳንቃ፡
ከቶ ምን አጣላን ድንበር ወይስ እቃ፡
እሽ ምን እንበል ንገሩን ሀቂቃ!?
የመንሀጁ ጉዳት አይሰማችሁም??
የህዝቡ መረበሽ አይታያችሁም!?
ወጣቱ ሲምታታ አያዝንም ውስጣችሁ!?
እሽ ምን እንሁን ምን እንበላችሁ፡፡
በአርሹ ባለቤት በአለሙ ጌታ፡
ነብዩን በላከው ለአለም ስጦታ፡
ለውህና ቀለምን አርሽን በፈጠረው፡
ሰማይና ምድሩን በሚያስተናብረው፡
ሞትንም ሀያትን በሰራው ፈጣሪ፡
ብቸኛ በሆነው በሌለው ተጋሪ፡
ልበላችሁና በምትፈሩት አምላክ በዛት በሲፈቱ፡
ይፈረጅ ጭንቃችን ለእርቅ ቤት ክፈቱ፡
ዳግም እንደገና ይድመቅ ታሪካችን፡
መጠራጠር ቀርቶ ይታደስ ፍቅራችን፡
ሀሳቡ ይቅለለን እርቅ ይሁን ግባችን፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አባቴ ተው ተነስ ወንድሜም ተው ንቃ፡
እናቴም እህቴም ያዘንሽው በሲቃ፡
ይሔ የፊትና በር ይዘጋልን በቃ፡
ተከፍቶ እንጣመር የአንድነት ሳንቃ፡
መንሀጃችን ሆኖ የእውነት መፍለቂያ፡
ምነው መሆናችን የጠላት መሳቂያ፡
ኢኽዋን ሱፍይ አህባሽ ተብሊግ ፎከረብን፡
እርስ በርስ ተባሉ እያሉ ዛቱብን፡
ጨነቀን ጠበበን እኛም አንገት ደፋን፡
ምን እንበል በአሏህ?መላ ቅጡ ጠፋን፡
ሀቁ ግልፅ ሆኖ በቁርአን በሱና፡
የምን ጭቅጭቅ ነው ምን ተፈጠረና፡
ከሐቅ በኋላ ምን መጣ እንደገና፡
አንዳችን ለአንዳችን እንደመተሳሰብ፡
ለምን አስፈለገ አቃቂር መሰብሰብ፡
#ኧረ_ተዉ_በአሏህ__!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ነብያቶች ሁሉ በአንድነት ሲላኩ፡
በተውሒድ በሱና ዑማውን ሲሰብኩ፡
አንድ ነበርኮ ግብና አላማቸው፡
ውዴታ ነው እንጂ ፀብ የለም ውስጣቸው፡
የነርሱ ተከታይ ነን ብለን በወሬ፡
ታዲያ ከየት መጣ ይሄ ጥርጣሬ?
ቆም ብለን እናስብ በቅጡ እናስተውል!?
ምን እየሰራን ነው እናስተንትን በውል፡
መከፋፈል ይቅር በውሃ ቀጠነ፡
ምን አገኘንና ፀባችን ፈጠነ!?
ምን አይነት አካሔድ መጣብን ዘንድሮ፡
ተከታይ ነን ብለን የጥንት የጧት ዱሮ፡
አድስ ፍልስፍና ሰርጎብን በጓሮ፡
የት እንደሆን እንጃ ታሽጎ ውሎ አድሮ፡
በቅርቡ መጣብን ዙሮ ተዟዙሮ፡
አሁንም ቅርብ ነው ተመካከሩበት፡
ይህ እምነት ነውና እንዳትቀልዱበት፡
እንወዳችኋለን እንለምናችሁ፡
እርቅ ፍጠሩና በደስታ እንያችሁ፡
ጥቂት ናችሁና ታሳሱናላችሁ፡
ሰማይን ዘርግቶ ምድርን ባሳመረው፡
ጨረቃን አድምቆ ኮከብን ባኖረው፡
ተራሮችን ተክሎ ምድርን ባረጋጋው፡
ብርሀን ተክቶ ጨለማን ባነጋው፡
ሰውና አጋንንትን በፈጠረው ጌታ፡
ተመስጋኝ በሆነው ሁሌ በጣት ማታ፡
በአርሹ ባለቤት ቁሜ ለመንኳችሁ ፡
ጃሒል መሀይሙ ሚስኪኑ ልጃችሁ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በኢብራሒም በኑህ በየዕቁብ ጎዳና፡
ጨለማን በናደው በብርሀን ፋና፡
ሞገስ በደረበው በስኬቱ ዳና፡
በዩሱፍ በየዕቁብ በሹአይብ በሁድ፡
በአዩብ በዙልኪፍል በኢሳም በዳውድ፡
በጀነቱ መንገድ በሙሳም የኢስሀቅ፡
መከፋፈል ይቅር አንድ እንሁን በሀቅ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
قال الله تعالي;
لقد كان في قصصهم عبرة لأولي الألباب.
#በኑረዲን_አል_አረቢ(12/01/1443)
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
--------—----------------------
#አንድ_እንሁን_በሀቅ
▬▬▬▬▬▬▬▬
ግራ ቀኝ እናስብ ይቅር መከፋፈል፡
አይጠቅመንምና የመልስ ምት ወንፈል፡
አንዳችን ለአንዳችን እንኳን ተጠላልተን፡
ወንድም ለወንድሙ እንኳን ተበላልተን፡
ጠላት ይፈልጋል እኛን ለመበተን፡
መታገስ ሲገባን መልስ ተሰጣጥተን፡
እንደ ተራ ነገር ጎራ ተለያይተን፡
ቂለ ወቃል የሚል ተራ ስም አውጥተን፡
ቀጥ ያለውን መስመር በስሜት ረስተን፡
የተውሒዱን ነገር ትተነው ዘንግተን፡
በራሳችን ጊዜ ጠላት አመቻችተን፡
ተንጋለን ቁመናል ለዘብህ አመችተን፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በፀጉር ስንጠቃ ከምንጠራጠር፡
ለቃላት ውርወራ ከምንቀጣጠር፡
ጠላት አንገት ይድፋ አንድነት እንፍጠር፡
የሱና ጠበቃ የሆንከው ወንድሜ፡
ስጋህ ከስጋዬ ደምህም ከደሜ፡
በመንሀጀ ሰለፍ እጂግ ተዋህዶ፡
በፍቅር አሳልፈን ሙቀትም በረዶ፡
አሁን ምን አገኘን ምን ተሰማ መርዶ፡
ሸይጧን በየት ገባ መሀባውን ንዶ፡
እጂግ ብዙ አመታት በፍቅር ተጋምደን፡
በአሏህ እገዛ ብዙ ስኬት ወልደን፡
ብዙ ጠላቶችን አፈራርሰን ንደን፡
በርካታ ጥመቶች ታግለን አስወግደን፡
አሁን ምን ተገኘ ምን መጣብን በኛ፡
ማን ተመለከተን ምን አይነት ቀበኛ፡
እንደት አይነት ቡዳ ምን መስሎ ገባብን፡
በፍቅር መካከል ጥላቻ ዘራብን፡
ጨነቀን በአሏህ ምን ማድረግ አለብን!?
እንባዬ ፈሰሰ እኔ በጣም ከፋኝ፡
ከማን ጋ ልሰለፍ ምን ቃል ልበል ጠፋኝ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ማን በምን ከፈተው የፊትናውን ሳንቃ፡
ከቶ ምን አጣላን ድንበር ወይስ እቃ፡
እሽ ምን እንበል ንገሩን ሀቂቃ!?
የመንሀጁ ጉዳት አይሰማችሁም??
የህዝቡ መረበሽ አይታያችሁም!?
ወጣቱ ሲምታታ አያዝንም ውስጣችሁ!?
እሽ ምን እንሁን ምን እንበላችሁ፡፡
በአርሹ ባለቤት በአለሙ ጌታ፡
ነብዩን በላከው ለአለም ስጦታ፡
ለውህና ቀለምን አርሽን በፈጠረው፡
ሰማይና ምድሩን በሚያስተናብረው፡
ሞትንም ሀያትን በሰራው ፈጣሪ፡
ብቸኛ በሆነው በሌለው ተጋሪ፡
ልበላችሁና በምትፈሩት አምላክ በዛት በሲፈቱ፡
ይፈረጅ ጭንቃችን ለእርቅ ቤት ክፈቱ፡
ዳግም እንደገና ይድመቅ ታሪካችን፡
መጠራጠር ቀርቶ ይታደስ ፍቅራችን፡
ሀሳቡ ይቅለለን እርቅ ይሁን ግባችን፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አባቴ ተው ተነስ ወንድሜም ተው ንቃ፡
እናቴም እህቴም ያዘንሽው በሲቃ፡
ይሔ የፊትና በር ይዘጋልን በቃ፡
ተከፍቶ እንጣመር የአንድነት ሳንቃ፡
መንሀጃችን ሆኖ የእውነት መፍለቂያ፡
ምነው መሆናችን የጠላት መሳቂያ፡
ኢኽዋን ሱፍይ አህባሽ ተብሊግ ፎከረብን፡
እርስ በርስ ተባሉ እያሉ ዛቱብን፡
ጨነቀን ጠበበን እኛም አንገት ደፋን፡
ምን እንበል በአሏህ?መላ ቅጡ ጠፋን፡
ሀቁ ግልፅ ሆኖ በቁርአን በሱና፡
የምን ጭቅጭቅ ነው ምን ተፈጠረና፡
ከሐቅ በኋላ ምን መጣ እንደገና፡
አንዳችን ለአንዳችን እንደመተሳሰብ፡
ለምን አስፈለገ አቃቂር መሰብሰብ፡
#ኧረ_ተዉ_በአሏህ__!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ነብያቶች ሁሉ በአንድነት ሲላኩ፡
በተውሒድ በሱና ዑማውን ሲሰብኩ፡
አንድ ነበርኮ ግብና አላማቸው፡
ውዴታ ነው እንጂ ፀብ የለም ውስጣቸው፡
የነርሱ ተከታይ ነን ብለን በወሬ፡
ታዲያ ከየት መጣ ይሄ ጥርጣሬ?
ቆም ብለን እናስብ በቅጡ እናስተውል!?
ምን እየሰራን ነው እናስተንትን በውል፡
መከፋፈል ይቅር በውሃ ቀጠነ፡
ምን አገኘንና ፀባችን ፈጠነ!?
ምን አይነት አካሔድ መጣብን ዘንድሮ፡
ተከታይ ነን ብለን የጥንት የጧት ዱሮ፡
አድስ ፍልስፍና ሰርጎብን በጓሮ፡
የት እንደሆን እንጃ ታሽጎ ውሎ አድሮ፡
በቅርቡ መጣብን ዙሮ ተዟዙሮ፡
አሁንም ቅርብ ነው ተመካከሩበት፡
ይህ እምነት ነውና እንዳትቀልዱበት፡
እንወዳችኋለን እንለምናችሁ፡
እርቅ ፍጠሩና በደስታ እንያችሁ፡
ጥቂት ናችሁና ታሳሱናላችሁ፡
ሰማይን ዘርግቶ ምድርን ባሳመረው፡
ጨረቃን አድምቆ ኮከብን ባኖረው፡
ተራሮችን ተክሎ ምድርን ባረጋጋው፡
ብርሀን ተክቶ ጨለማን ባነጋው፡
ሰውና አጋንንትን በፈጠረው ጌታ፡
ተመስጋኝ በሆነው ሁሌ በጣት ማታ፡
በአርሹ ባለቤት ቁሜ ለመንኳችሁ ፡
ጃሒል መሀይሙ ሚስኪኑ ልጃችሁ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በኢብራሒም በኑህ በየዕቁብ ጎዳና፡
ጨለማን በናደው በብርሀን ፋና፡
ሞገስ በደረበው በስኬቱ ዳና፡
በዩሱፍ በየዕቁብ በሹአይብ በሁድ፡
በአዩብ በዙልኪፍል በኢሳም በዳውድ፡
በጀነቱ መንገድ በሙሳም የኢስሀቅ፡
መከፋፈል ይቅር አንድ እንሁን በሀቅ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
قال الله تعالي;
لقد كان في قصصهم عبرة لأولي الألباب.
#በኑረዲን_አል_አረቢ(12/01/1443)
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬