"በትምህርት ቤቶች በየጊዜው የሚያገረሸው የኒቃብ ክልከላ ጉዳይ ቋሚ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ሲሉ ሼይኽ ኤሊያስ አህመድ ተናገሩ።
- ሀሩን ሚዲያ፥ ጥቅምት 19/2017
ሼይኽ ኤሊያስ አህመድ ኒቃብ የሚለብሱ ሙስሊም ተማሪዎችን ከትምህርት መታገድ አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም "በትምህርት ቤቶች በየጊዜው የሚያገረሸው የኒቃብ ክልከላ ጉዳይ ቋሚ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል።" ሲሉ ገልፀዋል።
አክለውም "ፊትን ከባዕድ ወንዶች መሸፈን ግዴታ መሆኑ የአብዛኛዎቹ ዑለማዎች አቋም ነው። ሆኖም ሴቶች ፊትና በማይሰጋበት ሁኔታ ለአስፈላጊ ጉዳይ ፊታቸውን ለወንዶች ማሳየት እንደሚችሉ የሁሉም የፊቅህ ሊቃውንት ንግግር ያሳያል።" ብለዋል
በዚህ መሰረት ተማሪዋ ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ስትገባ፣ ወደ ፈተና ማእድ ስትገባ፣ አጠራጣሪ ሁኔታ ሲኖር ወይም በማንኛውም ጊዜ ማንነቷን ማጣራትና ከመታወቂያዋ ጋር ማመሳከር ሲያሰፈልግ ፊቷን ገልጣ አሳይታ መልሳ መሸፈን ትችላለች። ያሉ ሲሆን «ሙሉ በሙሉ ተገልጠሽ ካልቆየሽ አትገቢም!» ማለት ግን ሀይማኖታዊ መብትን በግልፅ የሚጋፋ፣ ሴኪዩላሪዝም ጨምር የማይደግፈው… ምንም አግባብነት የሌለው የግለሰቦች ድርቅና ነው።" ብለዋል
© ሀሩን ሚዲያ