➾ደወይ የበዛብሽ !!
✍️ላስታውስሽ እህቴ በትንሹም ቢሆን
ደዋይ የበዛብሽ ስልክሽ ቢዚ እስኪሆን
የኢስላምን ባህር ያልገባሽ እንደሆነ
ላተቅረቡ ዚና ን ዘንግተሺው ከሆነ
ላስታውስሺ እህቴ በትንሹም ቢሆን
ወላሂ አይጠቅምሺም ተይ እንደዚህ መሆን
በረራ ማብዛትሽ ሰውን ተደብቀሽ
የአላህን ትዕዛዝ በጭራሽ እረስተሽ
ሊመክሩሺ ሲመጡ ምን አገባሽ ብለሽ
ፈዘኪር ማለቱን ጭራሹን ዘንግተሽ
ጭንቅላትሽ ዙሮ ሸይጧን ተቆጣጥሮሽ
ከወንድ ጋር ማውራት አራዳነት መስሎሽ
የነብዩን ሱና ፋራነት ነው ብለሽ
ዱኒያ ላይ የሚቀር አኽላቅ ተሸክመሽ
አረ እስከመቼነው አንቺ እንዲህ መሆንሽ
ተመሳሳይ ቦታ ሁል ጊዜ መውደቅሽ
ጉዞሽ የጂህልና ጥመት የሆነብሽ
እረተይ እህቴ አድምጭኝ ልንገርሽ
ደዋዩ ቢበዛ እውነት አይምሰልሽ
ለትዳር ለኒካህ አንዱም አያስብሽ
መሀላ ቢያበዛ ቃልም ቢገባልሽ
አትዘንጊው እህቴ ግቢ ውስጥ እንዳለሽ
ከእናት ከአባትሽ ከወንድም እርቀሽ
ክብርሺን ጠባቂ አንቺው እራስሺ ነሽ
በሀላሉ መንገድ እሱ እስከሚመጣ
ለምን ትሰሪያለሺ ቀብር እሚያስቀጣ
አትቅረቢ ወላህ ችግር ነው የሚያመጣ
ዱኒያም አያምርልሸ ቀብርም ያጠባል
ከጀነተል ፊርዶስ አብሮ ያወጣል
እህቴ ኢተቂላህ አንቺ ሙስሊም ነሽ
ከትናንት ተማሪ ዛሬ ግን ይብቃሽ
በረራን በማቆም ተውሂድን ልበሽ
ሰዎችን ቀይሪ አንቺም ቶብተሽ
በነብዩ ሱና ጉዞሺን አርገሽ
በዲንሽ ጠንካራ ጎበዝ ልጂ ከሆንሽ
እንቢታሺን ፈርቶ ማንም አይቀርብሽ
ለተራ ስሜቱ ላዳር የተመኘ
እንዲሁ ይቀራል ልቡም እንደዋኘ
አንተ ደሞ ስማኝ እባክህ ወንድሜ
እራት ካልጋበዝኩሽ ሻይ ቡናም እያልክ
መደወልክን አቁም አላህን ፈርተክ
10 አስሬ ወደድኩሽ አፈቀርኩሺ ያልከው
የልጂቱንም ልብ ግራ ያጋባከው
አንተ ወንድሜ ሆይ እስኪ ተው እረተው
ሴቶችን ማሳደድ አላማህ ላረከው
ወላሂ ኢተቂላህ አላህን አስታውሰው
ላተቅረቡ ዚና ማለቱን አትርሳው
አንዷ እንቢ ስትልህ ላንዷ ከመደወል
ለሀራም ለዚና በጣም ከመቸኮል
በጂህልና መንገድ ጉዞህ ከሚቀጥል
መርጠህ አንዷን አግባ ጊዜህ አይቃጠል
አስታውሳት እህትክን አውጣት ከጨለማ
ባንድላይ ደስ ይላል የተውሂዱ ማማ
እህትህ አትድከም አንተም አትሳነፍ
ገና በልጅ እድሜህ ለተውሒድ ተሰለፍ
እናም ወንድሜ ሰለፍዩ ወጣት
ነፍስህን ከመጥፎ አሁኑ ጠብቃት
ወጥተህ ከጨለማ በተውሒድ አድምቃት
ወጥተህ ከጨለማ በተውሂድ አድምቃት
✍️« 𝐵 ⁱⁿᵗ 𝐺𝑒𝑧𝑒 »