ኢየሱስ "አምላክ ነው!" እና ሰሞነኛ ወሬው!
ስራ ሲቀዘቅዝበት ማስታወቂያ እንደሚያበዛ ነጋዴ "ኢየሱስ አምላክ ነው" ብሎ ለሙስሊሞች ለማስረዳት ክርስቲያኖች ሰበብ በተገኘ ቁጥር ሁሉ ይደክማሉ። ከዛሬ 20 አመት በፊት የተደረገ ጥናትን በማቅረብ ሰሞኑን በሙስሊሞች ላይ ሊሳለቁ ከርመዋል።
ጉዳዩን እንደ አዲስ በማራገብ "ኢየሱስ አምላክ መሆኑን የሚያሳይ የተቀረፀ ፅሁፍ ነብያችሁ ሙሐመድ ከመወለዱ በፊት እስራኤል ውስጥ በቁፋሮ ተገኝቷል" በማለት ስሁት ሀተታ እየሰሩ ይገኛሉ። የስነ ቁፋሮ ባለሙያዎቹ እስራኤል ውስጥ በሚገኝ ሜጊዶ ወህኒ ቤት ላይ ባደረጉት ጥናት እስር ቤቱ ወለል ላይ በግሪክ ቋንቋ የተቀረፀ ፅሁፍ አግኝተዋል ¹
በዚህ ጥናት ወለል ላይ ሶስት ፁሁፎችን ያገኙ ሲሆን እነሱም፦
1. The Gaianus Inscription - ወለሉ እንዲሰራ ክፍያ የፈፀመውን ወታደር ስም እና የሰራው ባለሞያ ስም
2. The Akeptous Inscription - አምላክ ወዳድ የሆነችው አኬፕቶስ አምላክ ለሆነው ለኢየሱስ ክርስቶስ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ይህን ጠረፔዛ አቅርቧል - የሚል እና
3. The Women Inscription - ፕሪሚላ እና ሳይሪያካ እና ዶሮቲያ፣ እና በተጨማሪ ክረስቴን አስታውሱ - የሚል ፁሁፎች ተገኝተዋል።
ጥናቱ ያደረጉ ሰዎች በመጽሀፋቸው ሲያጠቃልሉ በገፅ 54 እንዲህ ይላሉ፦
“በከፋር ‘ኦትናይ’ የሚገኘው የክርስቲያን የጸሎት አዳራሽ መገኘቱ ከቆስጠንጢኖስ ዘመን በፊት በእስራኤል ምድር ክርስቲያን መገኘቱንና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በዋናነት በሥነ ጽሑፍ ምንጮች ሲዳሰስ በነበረበት ወቅት፣ በእስራኤል ምድር ለነበረው ክርስቲያን መገኘት ትልቅ ጠቀሜታ ያለው አርኪኦሎጂያዊ ማስረጃ ነው። በተጨማሪም የሕንፃው ጥናት በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከአይሁድ እምነት ይልቅ አረማዊ የሆነ የክርስቲያን ማኅበረሰብ መኖሩን ያረጋግጣል”
ልብ በሉ! ይሄ ኢየሱስ ካረገ ከ200 አመታት በሗላ ነው!!! በዚያን ወቅት ታዲያ “ኢየሱስ አምላክ ነው” የሚል ፅሁፍ መገኘቱ ምን ያስገርማል ታዲያ? ይህ ጥናት ምን አዲስ ነገር ኖሮት ነው? ከ 1800 አመት በፊት በክርስትያኑ ዘንድ የሚታወቁ የቤተክርስቲያን አባቶች/Church Fathers/ "ኢየሱስ አምላክ ነው" ብለው መጻፋቸው የሚታወቅ ነው። ታዲያ ምኑ ይሄ ይገርማል?
ምናልባት ከኒቂያ ጉባኤ (325) ጋር ተያይዞ ከሆነ ወቀሳው በኒቂያ ጉባኤ ወልድ “አምላክነቱ” በድምፅ ብልጫ ከመፅደቁ በፊት በአርዮስ እና ተከታዮቹ የነበረ ሃሳብ መኖሩን ከመግለፅ ውጪ የተለየ ትርጉም አይሰጥም።
አርዮስ ብቸኛ አምላክ አብ ነው ወልድ ግን የተወለደ፤ መጀመሪያ ያልነበረ ነው ሲል ያምናል። አባት ልጁን እንደማይቀድመው ሁሉ ወልድም አብን አይቀድምም የሚለው ሙግት የአርዮስ ሙግት ነበር። ስለዚህ በዚህ ጉባዔ አሪዮስን ተሳስተሃል፤ ከመጀመሪያም ጀምሮ ነበረ ፤ ከአብም ጋር እኩል አምላክ እንጂ ሁለተኛ አምላክ አይደለም ብለው ነው በድምፅ ብልጫ ያፀደቁት።
እናም "ኢየሱስ አምላክ ነው" የሚል ፅሁፍ በተገኘ ቁጥር ሙስሊሞች ላይ መሳላቁ ትርጉም አልባ የሆነና እናንተንም ትዝብት ውስጥ የሚከታችሁ ነው።
1- A CHRISTIAN PRAYER HALL OF THE THIRD CENTURY CE AT KEFAR ‘OTHNAY (LEGIO) Excavations at the Megiddo Prison 2005)