ቀንዳም ኑሮን በቀልድ ቀንበር
━━━━ ✦ ━━━━
✍ ዓለማየሁ ገላጋይ
'
ጎረቤቶቼ አብዛኛው እድሜያቸውን በትዳር ያሳለፉ አዛውንቶች ናቸው። ሰውየው 71፣ ሴቲቱ 68 ዓመታቸው ነው። እንደሚባለው ከሆነ አርባ ሁለት ዓመታት ያስቆጠረ የፍቅር አብሮነት አላቸው።
ሰሞኑን ከእነርሱ የትዳር ዘመን ጋር እኩል እድሜ የነበረው መኖሪያ ቤታቸው እንደሚፈርስ ተነገራቸው። በልዋጩም ኮንደሚኒየም ይሰጣችኋል ተባሉና 'ፕሮሰስ' ጀመሩ። ከ'ፕሮሰሱ' አንዱ ህጋዊ የጋብቻ ወረቀት ማውጣት ነው።
መንግሥት የካደባቸውን አርባ ሁለት ዓመት በልቦናቸው ይዘው በአጃቢ ወደ ጋብቻ አስፈፃሚ ድርጅት ሄዱ።
ሴትየዋ ፀጉራቸውን ተተኩሰዋል። በሀበሻ ልብስ ተሽሞንሙነው ከየጎረቤቱ በተጠረቃቀመ ጌጣ-ጌጥ ተንቆጥቁጠዋል። ሰውየውም ከወትሮው ለየት ያለ ሙሉ ልብስ ከነቄንጠኛ ባርኔጣው አድርገዋል።
ጋብቻ አስፈፃሚው ሹም ፊት ቀርበው ተፈራረሙ። ወደ ፎቶ መነሻው ክፍል ሲያመሩ ሞቅ ባለ የሙሽራ ዘፈን አጀብናቸው፦
"አይዞሽ ሙሽሪት አይበልሽ ከፋ
ሁሉም ያገባል በየወረፋ"
በዚህ መካከል አንድ ጓደኛዬ ወደ እኔ ጠጋ ብሎ፦
"ኧረ እኚህን ሴትዮ አንድ በላቸው" አለኝ።
"ማንን?" አልኩት
"ሙሽሪቷን"
"ምን አደረጉ?"
"እያለቀሱ ነው"
"ምን ሆነው?"
"ይህንን ወጌን እናቴ ሳታይ ሞተች እያሉ"
'ወግ ነው ለኮንዶሚኒየም ሲዳሩ ማልቀስ' እንበል ይሆን?
😂 😂 😂
━━━━━━━━━
📔 ኢህአዴግን እከሳለሁ!
🗓 ነሐሴ 2004 ዓ.ም.
📄 79 - 80
📖 📖 📖 📖 📖
@AdamuReta
@isrik