ሥለ እኛ
⎡ታመነ መንግስቴ ውቤ ነኝ—የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት ምሩቅ⎤
🎤በተለያዩ አጋጣሚዎች «ሚዲያ አራተኛው መንግስት ነው»ሲባል እሰማለሁ።
✅ንግርቱን የሚያረጋግጥ ሕገ-መንግስታዊ'ም ሆነ አዋጃዊ አንቀጽ መጥቀስ የሚችል ኢትዮጵያዊ ግን አጋጥሞኝ አያውቅም።
✍️ እውነት በኢትዮጵያ ዐውድ መገናኛዎችን(The Media) አራተኛ መንግስት የሚያሰኝ ሕጋዊ ማዕቀፍ አለ ወይ?
✍️በዓለም ዐውድ'ስ ከፈረንሳይ ፈላስፎች ዋናው እና የአብርሆት ዘመናቸው አሳቢ የነበረው ሞንትስኩ ከዘረዘራቸው ሶስቱ የመንግስት አካላት፦
ሀ.ሕግ አውጭው
ሁ.ሕግ አስፈፃሚው
ሂ.ሕግ ተርጓሚው
እንደ አንድ ሆኖ ብዙኃን መገናኛ የተጠቀሰበት አገር አለ ወይ?
🎤የኢፌዲሪ'ን መራሔ መንግስት ዐቢይ አሕመድ'ን ጨምሮ ብዙ ሰው «ጋዜጠኛ ደሃ ነው»ሲል እሰማለሁ።
✅ምን የሚሉት ያለ አዋቂ ንግግር ነው?
✍️ጋዜጠኞች እንደ ማንኛውም ፍጥረት ሰዎች ናቸው።ዐለምን የተሻለች ጥዑም እና ፍትሐዊ ለማድረግ ይተጋሉ።በዚህ ልፋታቸው ልክ ጸጋ የማካበት መብት አላቸው።አንድ ጠበቃ በአንዲት ጉዳይ(Case) አማካኝነት የሚያገኘውን ያህል ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ አንድ ጋዜጠኛ በአንዲት ጉዳይ(Case) ሰበብ ማግኘት አለበት።
✍የልቅ...!
ጋዜጠኝነት ከየትኛውም ንግድ በላይ አትራፊ ንግድ ነው።ጋዜጠኛ ሊሸጠው ያዘጋጀውን መረጃ ወይም ዕውቀት አልያም የመዝናኛ ዝግጅት ቀድሞ ጠግቦ እና ተደስቶበት ወደ ገበያ የሚያወጣ ቅን ነጋዴ ነው።
የትኛው ነጋዴ ነው ከረሜላ'ውን እየመጠጠ ከረሜላ ነግዶ የሚያተርፍ...!?
እኔ ግን ኦሮማይ'ን አንብቤ ስለ ኦሮማይ ስጽፍ ጠግቤ እንደማጎርስ ይቆጠራል።
«ሞያ»ው የሚደላችሁ በላይኞቹ አንቀጾች ላይ እንወያይባቸው❤
https://t.me/MisalieyegazetegninetSilttenaMak