በአዲስ አበባ የተሰረቁ የተለያዩ ዕቃዎችን እየተቀበሉ በሚሸጡ የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በመዲናዋ የተሰረቁ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስና የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችን በሚቀበሉ የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በመዲናዋ ልደታና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የተሰረቁ ዕቃዎችን በመግዛት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን ፥ የንብረቶቹ ማከማቻ የነበሩ ሱቆች ላይም እርምጃ ተወስዷል።
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3፣ ወረዳ 4 እና ወረዳ 7 አካባቢ አንዳንድ ሱቆች በስርቆት የሚመጡ የተለያዩ ዕቃዎችን እንደሚቀበሉ ተደርሶባቸዋል።
በመሆኑም ፖሊስ በክፍለ ከተማው መጋቢት 15 እና 16 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ ሱቆች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የተሰረቁ የሞባይል ስልኮች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ይዟል።
ፖሊስ በልደታ ክፍለ ከተማ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 80 የሞባይል ስልኮች፣ 24 ሲም ካርዶች፣ ሁለት ላፕቶፕ፣ አንድ ህገ-ወጥ ሽጉጥ እና በርካታ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ተይዘዋል።
ከተያዙት ዕቃዎች ጋር 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ኮሚሽኑ በመግለጫው አመልክቷል።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማም መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ አካባቢዎች በንግድ ሱቆች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 618 የሞባይል ስልኮች፣ አምስት ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ 45 ሲም ካርዶች እና ሌሎችም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ተይዘዋል።
በተመሳሳይ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ያላቸው ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።
ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው የንብረት ዓይነቶች በተለያየ አጋጣሚ የጠፋባቸውና የተሰረቀባቸው ባለንብረቶች ባስመዘገቡት መሰረት እየተመሳከረ በመረጋገጥ ላይ መሆኑ ታውቋል።
በአዲስ አበባ በስፋት እየተስተዋለ የመጣውን ሌብነትና ዘረፋ ለመቆጣጠር በቀጣይም ቁጥጥሩን በማጠናከር እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
@Addis_Tv