ተመራማሪዎች በጡት ካንሰር እጢዎች ውስጥ ያሉ ሴንትሮሶሞችን (Centrosomes) በጥልቀት መተንተን የሚችል አዲስ የ-AI ሲስተም አበለፀጉ
🖱️ተመራማሪዎች በሴል ክፍፍል ውስጥ ወሳኝ ሚና ያላቸውን ሴንትሮሶሞች (Centrosomes) በመላው የጡት ካንሰር እጢዎች ላይ መመርመር የሚያስችል የ-AI ቴክኖሎጂ ይፋ አድርገዋል። በሴንትሮሶሞች ላይ የሚታዩ ያልተለመዱ ሁኔታዎች ከካንሰር ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ከ100 ዓመታት በላይ በሳይንቲስቶች ዘንድ ቢታወቅም የቅርጾቹ ጥቃቅንነት እና ውስብስብነት ምክንያት እስካሁን ድረስ ጥልቅ ጥናት ለማድረግ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል።
🖱️አዲሱ የ-AI ሲስተም በጡት ካንሰር ታካሚዎች ውስጥ የሚገኙ ከ330,000 በላይ ሴንትሮሶሞችን የመረመረ ሲሆን ከዚህ ቀደም እንደ አንድ አይነት እክል ይታይ የነበረው ሁኔታ በውስጡ ሁለት የተለያዩ ሂደቶች እንዳሉት ለይቷል። ከእነዚህም አንደኛው ሂደት ከእጢው ከፍተኛ አደገኛነት (Aggressiveness) እና ከዝቅተኛ የመዳን እድል ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ተረጋግጧል።
🖱️ይህ አሰራር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ከዚህ ቀደም በሰው ልጅ ምርመራ የማይደረስባቸውን ረቂቅ የህክምና ቅጦች (Patterns) በትክክል ለይቶ ለማወቅ እና ለካንሰር ህክምና አዲስ አቅጣጫ ለመክፈት ያለውን ትልቅ አቅም ያሳያል።
🤩 @AddisIntel