✴️ በ-OpenAI እና 🤶 Anthropic መካከል ያለው ከፍተኛ የገበያ እና የቴክኖሎጂ ፉክክር ተባብሶ ቀጥሏል
በ-AI ገበያ ውስጥ ዋነኛ ተፎካካሪ የሆኑት OpenAI እና Anthropic የዋጋ ቅነሳን አዳዲስ የገቢ ምንጮችን እና የአክሲዮን ገበያ (IPO) ዝግጅትን ጨምሮ በበርካታ መስኮች ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል። OpenAI በቅርቡ የ-GPT-5.6 Sol API ዋጋን ለሚቀጥሉት 3 ወራት ከ20% በላይ የቀነሰ ሲሆን በ-ChatGPT ውስጥ ማስታወቂያዎችን ማካተት ጀምሯል እንዲሁም የ-Inference ፍጥነቱን በ14 እጥፍ አሳድጓል።
➡️በሌላ በኩል Anthropic ዓመታዊ ገቢው 65 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን የራሱን ብጁ ቺፖች (Custom chips) የማምረት ስራ ጀምሯል
🔺Anthropic በመጪው ጥቅምት ወር የ2 ትሪሊዮን ዶላር ግምት ይዞ ወደ አክሲዮን ገበያ (IPO) ለመግባት እያቀደ ሲሆን የ-OpenAI የ-IPO እቅድ ግን ወደ 2027 ዓ.ም ተራዝሟል
🔺እንደ Ramp መረጃ ከሆነ በአሜሪካ የድርጅቶች አጠቃቀም (Enterprise adoption) ረገድ Anthropic በ43.5% ድርሻ OpenAIን (39.7%) እየመራ ይገኛል
🔺ይሁን እንጂ በተጠቃሚዎች ብዛት OpenAI በየሳምንቱ 900 ሚሊዮን ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን ይህም የ-Anthropicን ወርሃዊ 245 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች በከፍተኛ ልዩነት ይበልጣል
ይህ የገበያ እንቅስቃሴ የ-AI ኢንዱስትሪው ከተጠቃሚዎች ቁጥር ፉክክር ባለፈ የኮርፖሬት ገበያን እና የትርፋማነት አቅምን ወደ መቆጣጠር እያመራ መሆኑን ያሳያል።
🤩 @AddisIntel