ወይ ያ'ኔ
ሰላም ተሸርሽሮ መሰረቱን ሲያጣ
የስልጣን እርካቡ ታሪክን ሲተካ
ጸሀይ ነዉ ያልነዉ ቀን ዳምኖ አዘነበ
ዘርም ተበላሸ ሰብልም ረገፈ
ወይ ያ'ኔ ያልነዉ ቀን ወይዘንድሮ ሆነ
ስሙን በመለወጥ ታሪክን ደገመ
በልጽገን አሽተን አፍርተን የኖርነዉ
ለካስ እየረገፍን ወድቀን ተነስተን ነዉ
እንደዘመን እማ እንደ ታሪክማ
እንደ ነገስታቱ እንደ ሀገር ጀግና
ታቦቱን አዉጥተዉ ድል የተቀናጁ
ደማቅ ታሪክ ጽፈዉ ሀገርን ያቆዩ
እልፍ ሰማእታት ነግሰዉ ነበር ያኔ
ያኔ ጥሩ ነበር ዛሬ እንበል ወያኔ
ለኛም ገርሞናል ሆነና ብሂሉ
እኛም አልገባንም ከተነሳንበት ወድቃቹሀል ሲሉ
😁😁😁😁😁😁😁😁
እንቁ ማርያም (መባ)
ሰላም ተሸርሽሮ መሰረቱን ሲያጣ
የስልጣን እርካቡ ታሪክን ሲተካ
ጸሀይ ነዉ ያልነዉ ቀን ዳምኖ አዘነበ
ዘርም ተበላሸ ሰብልም ረገፈ
ወይ ያ'ኔ ያልነዉ ቀን ወይዘንድሮ ሆነ
ስሙን በመለወጥ ታሪክን ደገመ
በልጽገን አሽተን አፍርተን የኖርነዉ
ለካስ እየረገፍን ወድቀን ተነስተን ነዉ
እንደዘመን እማ እንደ ታሪክማ
እንደ ነገስታቱ እንደ ሀገር ጀግና
ታቦቱን አዉጥተዉ ድል የተቀናጁ
ደማቅ ታሪክ ጽፈዉ ሀገርን ያቆዩ
እልፍ ሰማእታት ነግሰዉ ነበር ያኔ
ያኔ ጥሩ ነበር ዛሬ እንበል ወያኔ
ለኛም ገርሞናል ሆነና ብሂሉ
እኛም አልገባንም ከተነሳንበት ወድቃቹሀል ሲሉ
😁😁😁😁😁😁😁😁
እንቁ ማርያም (መባ)