ውስጣዊ ማንነትን ማወቅ-2
....✍ካለፈው የቀጠለ
ይሁን እንጂ ይህን እንድታደርጉ አልተበረታታችሁም፤ እንድትጠይቁ፣ ተመራምራችሁ እውነትን በራሳችሁ እንድታገኙት የሚነግራችሁ ማንም የለም - ምክንያቱም አማጽያን ከሆናችሁ ውሸት በሆነው ነገር ላይ ሁሉ አደጋ ትፈጥራላችሁ፡፡ ወላጆቻችሁ፣ ማህበረሰቡ፣ እናንተ ራሳችሁም አደጋ የሌለበት ኑሮ መኖር ትፈልጋላችሁ:: ደህንነቱ የተጠበቀ ኑሮ የሚገኘው በማስመሰልና በፍርሃት ነው:: የትምህርት አላማ በነፃነት ያለ ፍርሃት እንድንኖር መርዳት ነው፣ አይደለም እንዴ? ፍርሃት የሌለበት አካባቢ ለመፍጠር በእናንተም ሆነ በመምህራችሁ በኩል ትልቅ ጥረት ይጠይቃል፡፡
ይህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ - ፍርሃት የሌለበት አካባቢ ለመፍጠር ምን የተለየ ነገር እንደሚያስፈልግ ታውቃላችሁን? ዓለም ማብቂያ በሌላቸው ጦርነቶች ተይዟልና፣ ስልጣን በሚፈልጉ ፖለቲከኞች እየተመራ ነውና ያን እጅግ ልዩ የሆነ ነገር መፍጠር አለብን፡፡ ዓለም ስልጣን በሚፈልጉና ይህንንም ለማግኘት እርስ በርስ በሚናቆሩ ጠበቆች፣ ፖሊሶችና ወታደሮች ተሞልቷል:: ዓለም አብዷል፤ ፍፁም ግራ ተጋብቷል፤ ኮሚኒስቱ ካፒታሊስቱ ጋር
እየተዋጋ ነው ፣ ሶሻሊስቱ ሀለቱንም ለመቋቋም እየጣረ ነዉ፤ አንዱ ስልጣንና ምቾት ለማግኘት ከአንዱ ጋር ይጣላል። ዓለም በሚጋጩ እምነቶች በቡድንና በመደብ ልዩነቶች ፣ በሃገር ወዳድ ፅንፈኞች፣ በማይረቡ ጭካኔዎች ተከፋፍሏል፡፡ ከእንዲህ አይነቱ አለም ጋር እንድትጣጣሙ ነው እየተማራችሁ ያላችሁት፡፡ ከዚህ አጥፊ ማህበረሰብ ስርአት ጋር እንድትጣጣሙ እየተበረታታችሁ ነው:: ወላጆቻቹ ይህንን እንድታደርጉ ይፈልጋሉ፤ እናንተም ይህን ትፈልጋላችሁ።
የትምህርት ተግባር ምንድነው? ይህንን የበሰበሰ ማህበራዊ ደንብ እንድታከብሩ ማድረግ ወይስ የምታድጉበትንና አዲስ ማህበረሰብ፣ አዲስ ዓለም የምትፈጥሩበትን ምሉዕ ነፃነት መስጠት ነው? እኛም ይህን ነፃነት እንድትጎናፀፉ እንፈልጋለን - ነገ ሳይሆን ዛሬ፤ አለበለዚያ ሁላችንም እንጠፋለን፡፡ እውነት የሆነውን እንድታውቁ፣ ብልህ እንድትሆኑ፣ዓለምን ተጋፍጣችሁ መገንዘብ እንድትችሉ፣ በውስጣችሁ በስነ ልቡና ረገድ ያለማቋረጥ እንድታምፁበት አንድ የነፃነት ድባብ መፍጠር አለብን:: እውነትን የሚያገኘው አንድ የሆነ ልማድን የሚከተል ሳይሆን በዚያ ልማድ ላይ ያለማቋረጥ የሚያምፅ ነው:: ያለማቋረጥ ስትጠይቁ፣ ያለማቋረጥ ስታስተውሉ፣ ያለ ማቋረጥ ስትማሩ ነው እውነትን፣ እግዚአብሔርን ወይም ፍቅርን ማግኘት የምትችሉት:: ከፈራችሁ መጠየቅ፣ ማስተዋል፣ መማር፣ በጥልቁ ንቁ መሆን አትችሉም:: እናም የትምህርት ዋነኛ ተግባር መሆን ያለበት የሰውን አስተሳሰብ፣ ሰብአዊ ግንኙነትና ፍቅር የሚያጠፋውን ያን ፍርሃት ከውስጥም ከውጭም . ማስወገድ ነው::
ምንጭ ፦ ውስጣዊን ማንነት ማወቅ (ክሪሽና ሙርቲ )
ትርጉም ፦ ተስፋሁን ምትኩ
@Zephilosophy