የአማራ ክልል ዳኞች ያለመከሰስ መብት በህግ ጥበቃ አገኘ!!
.................
ባሕር ዳር: የካቲት 07/2017 ዓ.ም
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የአራተኛ ቀን ጉባኤውን እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ በአራተኛተኛ ቀን ውሎው በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በኩል የቀረቡትን አምስት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል። ካጸቃቸው ረቂቅ አዋጆች መካከል የአማራ ክልል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 281/2014 ለማሟላት የቀረበው አንዱ ነው። ይህ አዋጅ በማሟያነት ከያዛቸው ድንጋጌዎች አንዱ የክልሉ ዳኞች ያለመከሰስ መብት ይገኝበታል።
እንደሚታወቀው የክልሉ ዳኞች ያለመከሰስ መብት ከዚህ በፊት ለዚሁ ምክር ቤት ለሁለት ጊዜ ያህል ቀርቦ ተቀባይነት እንዳይኖረው የተደረገ መብት ነው። የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበርም የዳኞች እስራት እና ወከባ እንዲቆም፣ የክልሉ የዳኝነት ነጻነት በዘላቂነት እንዲከበር እና ከምንም በላይ ደግሞ የዳኞች ያለመከሰስ መብት በህግ ጥበቃ እንዲሰጠው የሚመለከታቸውን አካላት በተደጋጋሚ ሲጠይቅበት የነበረ ጉዳይ ነበር። ይህንን የማኅበሩን ጥያቄ መነሻ በማድረግም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን(ኢሰመኮ) ጨምሮ በርካታ አካላት ይህ መብት በህግ ጥበቃ እንዲያገኝ ለክልሉ መንግስት ሲያሳስቡበት የቆየም ጉዳይ ነው። እናም የክልሉ ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሔደው ጉባኤ ለዚህ ጥያቄ መልስ ሰጥቷል።
የዳኞች ያለመከሰስ መብት በህግ ጥበቃ ማግኘቱ በዳኞች ላይ የሚፈጸመውን እስር፣ እንግልት እና ወከባ በመጠኑም ቢሆን እንደሚቀንሰው እና ለክልሉ የዳኝነት ነጻነት መከበርም ዋስትና የሚሰጥ ስለመሆኑ ማኅበሩ ያምናል። ይህ መብት በህግ ከለላ እንዲሰጠው በርካታ አካላት ርብርብ ያደረጉ ሲሆን ይህንን ጥያቄ በባለቤትነት ተቀብሎ የህግ ማሟያ አዘጋጅቶ በርካታ አካላትን በሚገባ አስረድቶ ለምክር ቤት በማቅረብ ለውጤት ያበቃውን አዲሱን የጠቅላይ ፍ/ቤት አመራር ማኅበሩ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረበ የክልሉ ዳኞችንም እንኳን ደስ አላችሁ ማለት ይፈልጋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት ሹመታችሁ ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ የጸደቀ 9 የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ደብረ ማርቆስ ምድብ ችሎት፣ 46 የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች እና 171 የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች ማኅበሩ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላችሁም መልካም ምኞቱን ይገልጻል።