#ዝክረ_ዓድዋ ፪
አሁን ባለው የአለም ስርዐት ውስጥ ለሀገራት ሀያልነት ቁልፍ ሚና ከሚጫወቱ ነገሮች መካከል የስለላ ተቋሞቻቸው ግንባር ቀደምት ናቸው።
የሁለተኛውን የአለም ጦርነት ውጤት የቀየረችው ቅንጣት የምትመስል ነገር ግን ትልቅ ትርጉም ያላት የስለላ ተግባር ናት። ዓድዋ ላይም የሆነው ይኸው ነው!!
ብዙ ባንዳ ሰላዮችን ወደ ምድረ አቢሲኒያ በገፍ ያሰማራችው ኢጣልያ...በአንድ ሀገር ወዳድ ብልህ ኢትዮጵያዊ የተነሳ ከጦርነት አውድማው በፊት ተረታች...
ኢጣልያ የተሸነፈችው ዓድዋ ላይ ቢሆንም ለዓድዋው ድል መሰረት ከጣሉ አያሌ ሁነቶች መሀል በዛን ዘመን ሰለጠኑ የሚባሉ አካላት ላይ የወሰድነው የስለላ ብልጫ ነበር።...
ይህ አንድ ለእናቱ የሆነው የዓድዋ ጀግናችን ባሻ አውኣሎም ይባላል...
ባሻ አውኣሎም ባሻ አውአሎም ሐረጐት - (ያልተዘመረላቸው ኢትዮጵያዊ ጀግና)
ባሻ አውአሎም በኤርትራና በትግራይ የሚመላለሱ ነጋዴ ነበሩ፡፡
ቀደም ሲል ራስ አሉላ ኢጣሊያኖችን እየሰለሉ እንዲነግሯቸው ፣ የኢትዮጵያን ጦር ምስጢር ደግሞ አሳስተው እንዲጠቁሟቸው ከባሻ አውአሎም ጋር ተስማምተው ነበር፡፡
የምኒልክ ጦር ጣልያን ከምሽጉ እንዲወጣ...የተዘየደው ነገር በኢጣሊያኖች የሚታመን የኢትዮጵያ ሰው በኩል የተሳሳተ መረጃ በማቀበል ከምሽጋቸው ወጥተው ውጊያውን እንዲጀምሩ ማድረግ ነበር።
ይህንንም ለጀግናው የጦር አለቃ ራስ አሉላ አባነጋ አማከሩና...ራስ አሉላ ቀድሞ ለራሳቸውና በኋላም ለጣሊያን ስለላ ይሰሩ የነበሩ አውዓሎም የተባሉ ነጋዴ...ጣልያንን መረጃ እንዲያስቱ በእርቅ ከአፄ ምኒልክ ጋር እንዲገቡ ተደረገ።
አፄ ምኒልክም ይቅርታ አድርገውላቸው እቴጌ ጣይቱም በእህል ውሀ ሰበብ
"አውአሎም ይህ የምትበላው እንጀራ ቁርባን ነው"
ብለው በአፄ ምኒልክና በመኳንንቱ የተዘጋጀውን ወጥመድ እንዲፈጽሙ አስማሏቸው።
ለጣሊያኑ ጄነራል
'ኢትዮጵያኖች በእለተ እሁድ ቤተክርስቲያን የመሳለም ልማድ ስላላቸው ፤ የካቲት 23 ሰንበትም ብዙው ወታደር አክሱም ፅዮን ለመሳለም ስለሚያቀና የቀረውም ምግብ ፍለጋ በመበተኑ ንጉሠ ነገሥቱ ብቻቸውን ይሆናሉ ...
በጠዋት ማጥቃቱ ቢጀመር ድሉ ያለምንም ጥርጣሬ የጣሊያን ይሆናል"
ብሎ አሳመነ።
በዚህም የጠላት ጦር ንጉሠ ነገሥቱን ብቻቸውን ሊወጋ ቋምጦ ሲገሰግስ ከዐድዋ ሠፈር ተቃረበና ጧት በዐሥራ አንድ ሰዓት ርችት አሰማ።
የምኒልክም ሠራዊት አድፍጦ ሲጠባበቅ አድሯልና አፀፋውን መለሰ...በዚህ ጊዜ አፄ ምኒልክ የዐድዋን ጦርነት ከፈቱ።
ጦርነቱ ሲፋፋም አውአሎምና ጓደኛው ወደ ወገናቸው ጦር ሲቀላቀሉ ያየና ነገሩ የገባው ጄኔራል ባሪያቴሪ
"አውዓሎም አውዓሎ
ም
"
እያለ ሲጣራ አውዓሎም ሰም
ተ
ው
"ዘወአልካዩ እያ
ውዕ
ለኒ"
ብለው አፌዙበት። (በዋልክበት አያውለኝ እንደማለት ነው)
ባሻ ኣውኣሎም ኩርፊያ ከሀገር ፍቅር ፤ ገንዘብ ከነፃነት ያልበለጠባቸው ታላቅ የሀገር ኩራት!
እንካ የሀገር ጀግና ፤ እንካ ባለውለታ
ተኩሶ ብቻ ሳይሆን ፤ ሰልሎ ጠላት የሚመታ
ባሻ #አውኣሎም
እናመሰግናለን እምዬ ምንሊክ
እናመሰግናለን እቴጌ ጣይቱ
እናመሰግናለን ሴት ወንድ አርበኞቻችን
እናመሰግናለን ባሻ ኣውአሎም#ዓድዋ
@Astu_Official_Crypto