ገምሃልያ
....ክፍል 3 .....;
መልካም ንባብ
ምን አይነት ኖሮ እንደምትኖሪም አላውቅም እኔ አንቺ ላይ በማየው ነገር መፍረድ አልችልም አላውቅሽም ግን... ግን እማውቀው አንድ እውነት አለ ምንም አይነት ችግር ቢያጋጥምሽ በህይወትሽ እንደሲጋራው ጭስ ሆነሽ ወደላይ መውጣት አሊያም ያለቀውን የከሰለውን አመድ ሆነሽ ወደ ትቢያ መውደቅ! ምርጫው ያንቺ ነው አልኩና በእጄ የነበረውን ሲጋራ ወደሷ ዘረጋሁ ሲጋራውን ተቀብላኝ መሬት ላይ አስቀመጠችው።
እጇን ለሰላምታ ዘርግታልኝ ፅናት እባላለው አለችኝ የዘረጋችው እጇን ጨብጬ ሰላም አልኳትና ብዬ ስሜን ነግሪያት ቦታዬ ላይ ተቀመጥኩ። ያመጣሁትን መፅሃፍ ገፆች ገልጬ ማንበብ ቀጠልኩ ብዙም ሳይቆይ ግን ፅናት መናገር ጀመረች። ብዙ ግዜ ሰው ራሱ እስካልነገረኝ ድረስ በግድ እንዲያወሩ ማድረግ ብዙም ደስ አይለኝም። ምን እንደሚያስገርመኝ ታውቃለህ አለችኝ ወደሷ ዞሬ እያየኃት ምን አልኳት። ታውቃለህ ህይወት ለኔ በጣም በፈተና የተሞላች ናት አንድም ቀን እንኳን ለራሴ ኖሬ አላውቅም ሁሌም ለታድኤል ስል ነበር እምኖረው እሱ ግን እሱ....ግን.... አለችና ትካዜ በተቀላቀለበት ሃሳብ ውስጥ ተዋጠች።
ከታድኤል ጋር ለመጀመሪያ ግዜ የተዋወቅንበትን ቀን መቼም አልረሳውም አስታውሳለው እለቱ ቅዳሜ ነበር ጠዋት ከስራ እንደወጣው ሜክሲኮ አከባቢ የምትገኝ ሃናን የምትባል ውድ ጓደኛዬ ቤት ሄጄ ከሷ ጋር ስንጨዋወት አረፋፍደን ምሳ ሰአት አከባቢ ወደቤቴ ልሄድ ተሰናብቻት ወጣው። ሜክሲኮ አከባቢ ወደ ፒያሳ የሚወስደኝን ታክሲ የምይዝበት ቦታ ሄድኩ ታክሲዎቹ ምን እንደነካቸው አላውቅም አለወትሮዋቸው ጥፍት አሉ። ብቻዬን በዛ በጠራራ ፀሃይ ታክሲ መጠባበቅ ጀመርኩ የፀሃዩ ብርታት ነው መሰለኝ ራሴን ያመኝ ጀመር በዚ አጋጣሚ አንድ ረዘም ብሎ ደንደን ያለ ሰውነት ያለው ሰው ከኃላዬ መጥቶ ቆመ ደንገጥ ብዬ ዞሬ አየሁት ጥቁር ኮፍያ እና መነፅር አድርጓል ሰውነቱ የለበሰውን ነጭ ቲሸርት ውጥርጥር አድርጎታል እሚያምር ችምችም ያለ ፂም አለው እንዳየሁት ሌቤ ደንገጥ ሲል ታወቀኝ። ሳላስበው ብዙ እንዳፈጠጥኩበት ሲገባኝ እንደማፈር እያለኩ ዳግም ጀርባዬን ሰጥቼው ቆምኩ። ሁለታችንም ፊትና ኃላ ሆነን ታክሲዎቹን ብንጠብቅን ምንም ሊመጡ አልቻሉም ነዳጅ ጠፍቶ ይሆናል እንዲ የጠፉት አልኩ በልቤ። ወደኃላ ዞሬ አየት አድርጌው ተመለስኩ ላወራው ፈለግኩ ግን ፈራሁት ሁሉ ነገሩ ልብ እሚያስደነግጥ ግርማ ሞገስ አለው። ድንገት ሳላስበው ከኃላዬ ጎርነን ያለ ድምፅ ዛሬ ፀሃይዋ ከነቤተሰቦቿ ነው መሰለኝ ተጠራርታ የመጣችው አለኝ ዞር ስል እሱ ራሱ ነበር ፈገግ ብዬ እንደመሳቅ እያልኩ አው ዛሬ ሃይለኛ ሆናለች ምን እንደታያት አልኩት እሱም መልሶ እየሳቀ ከታላቅ እህቷ ጋር ነው መሰለኝ የመጣችው አለኝ። ምን ለማለት እንደፈለገ ባይገባኝም ከት ብዬ እንደሞኝ ሳቅኩ። የኔ አሳሳቅ እሱንም አሳቀው መሰለኝ እሱም ሳቀ። ሲስቅ ጥርሶቹን በጨረፍታ አየኃቸው በጣም ያምራሉ በጣም ማረከኝ ያደረገው ጥቁር ኮፍያና የፀሃይ መነፅር፤ ቅርፅ የተበጀለት ችምችም ባለው ፂሙ መሃል ጥርሶቹ ፍልቅቅ ብለው ሲታዩ ልብን ያሸፍታሉ የደስደስ ያለው ደስ እሚል ሰው ይመስላል። እሱን ሳስብ ራስምታቴ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ረስቼው ነበር ድንገት ትልቅ ህመም ተሰማኝ ቀጥሎ የተፈጠረውን አላውቅም ራሴን ስቼ ወድቄ ነበር ወደራሴ ተመልሼ ስነቃ ጣላ ያለበት ዛፍ ስር ተኝቻለው መጀመሪያ የየሁት የእሱን ፊት ነበር! ቀና አድርጎኝ የያዘውን ሃይላንድ እላዬ ላይ እያርከፈከፈልኝ ነበር ፊቱ ላይ ድንጋጤ ይነበባል። መንቃቴን ሲያይ ደና ነሽ እሙዬ ምን ሆነሽ ነው
ይቀጥላል....
@Logout17