ከአሁኑ ከተሜ መንፈስ ሪቮ ወይም ሪፎርም ጠብቄ አይደለም እርግጥ።
➺ ለምን ይመስላችኋል የማልጠብቀው?
እዚህ ጋ የሚላን ኩንዴራን "የተደረገባችኹን በእኔ በኩል እዩ" የምትል 'The Book of Laughter and Forgetting ' መፅሐፍ አነሳላችኋለሁ።
በዚህች መፅሐፍ ውስጥ አንዲት ስም የሌላት ከተማ አለች። እሱ የፃፈላት የቼኳ prague መጠሪያ የሌላት፤ ስም ስላልወጣላት አይደለም— ከተማዋ ስሟን ስለረሳችው እንጂ። የረሳችውም በ'ንዝህላልነት ወይም በስንፍና ስለተገኘች አይደለም፤ ይልቁንም በታሰበባትና በተደረገባት የታሪክ እጥበት ምክንያት እንጂ
በ'ስቶሪው' ውስጥ የሶቭየት ታንኮች ስም በሌላት ከተማ፡ በገቡና በተቆጣጠሩ በጥቂት አመታት ውስጥ የወሰዱት እርምጃም... ነባርና ብሉይ ስሞችን፥ ብራንዶችንም በሙሉ መቀየር ነበር።
ይኼም የተረደገው፤ "ስም" በራሱ ያለፈውን አስታውሶ ክትያ(ተከታይ) ጥያቄዎች፥ ትዝታዎችና መረሳት ላለባቸው (በገዢው ድምዳሜ አስፈሪ የሆነበትን) ሁነቶች... ዳግም ለመነሳት መሠረት ስለሚጥል ነው።
አስቀድሞ ስም በመፋቅ ውስጥ ስም አልባ፡ ባዶ ታሪክ ብቻ ወደ ጎዳና ይተዋል። የተጣለ የታሪክ ክፍል ብዙ ጊዜ ከትውስታ ዓለም የራቀ ነው። ኩንዴራ እንዲህ ይላል
«... ታሪኩን የማያስታውስ ሕዝብ ለመገዛት ይመቻል።»
"ነባር መንደሮችና ግድግዳዎቻቸው ለምን ፈረሱ?" ምናምን አይደለም አሁን የዚህ ሁሉ ነገር መነሻዬ። አንድ ሰው መጥቶ ምን ግድግዳ አለንና? ቢለኝ የምመልሰው ላይኖረኝ ይችላል። ግራፊቲይ፥ ግድግዳ፥ ቤትና ሕንፃዎች ምናምን ሳነሳ bulky የኾነን ሐሳብ አንገት ለመያዝ ነው። የአያቶቻችሁን አብረቅራቂ ወዝ ያያችሁበት ግንብ ማጣት በኾነ መልኩ "የሰውነት ንግስናን" መንጠቅም አለው የሚለውን ለመናገር እየሞከርኩ ነው። ዛሬ ይሁዲና ደች እየተጫወተ አብሮ ቢራ የሚጠጣው በትላንት አጥሩና ደሙ ሳይካካድ ነው፤ ወደፊት እየተራመደ... ፊቱን ወደኋላ በማቄም አዙሮ የሚኼድ ቡድን ደግሞ በ'ነሱ ተቃራኒ አጠገባችሁ ታገኛላችሁ።
የእኛ ከተማ ግን ምን አጠፋ? ትላልቅ ከተሞች በነባር ከተሞች ፍርስራሽ ላይ
ተገንብተዋል። ሊካድ የሚችል አይደለም። የእኛ ስራ መንፈሱ ግን የመታደስ ነው የመውረስ?
ድርሳነ ኩንዴራ ድጋሜ ምን ይልሃል The struggle of Man against Power is the struggle of Memory against Forgetting.⁴ የ'ኔ ትውልድ የ'ዚህ ሂደት ውጤት ማሳያ መኾን ይችላል። ከእራሱና ከትላንቱ ጋ ያለው 'ርቀት የሚያሳዝንና የሚያስደነግጥ ነው።
ሰው ስለትላንት የሚያነሳው የሚኖረው በታሪክ ውስጥ ስለኾነ ነው። ታሪክ መንጠቅ መኖሪያ የማሳጣት አስጸያፊ ተግባር ነው። ታሪክም፥ ቁስም መንጠቅ ምን አይነት ደረጃ ያለው ተግባር እንደኾነ ደግሞ፤ ማኪያቬሊ ይወቅ¡
እንደ ጥቅል እውነታ ካየነው ያለፈው ኹኔታና ገሃዳችን አሁን ከምንኖርበት ከእኛ ዛሬ ጋ በእጅጉ የተሳሰረ ነው። ስለዚህም ያለፈው ከእኛ ጋር ነው ማለት እንችላለን። ያለፈው እኛ ውስጥ ነው። እኛም ያለፈውን አሁን እየኖርን ነው።
ነገር ግን እኛ በዚኽ ጊዜ የተገኘን ትውልዶች፤ ይኽን ለማለት መታደላችንን እጠራጠራለሁ። እኛ የምንኖረው በታሪክ ውስጥ ነው? አይመስለኝም። እኛ የታሪክም ኾነ የግድግዳ(ወኔ፥ የነፃነት መንፈስ፥ ማንነት...) እርክክብ ያልተደረገልን ትውልድ እንደሆንን ነው ያለነው። ስለዚህም በቀውስ ውስጥ ተገኝተናል። ታዲያ ራሱን ያላዳነ ትውልድ አብዮት ከየት ያመጣል ብዬ ልጠብቅ?
"የተካደ ትውልድ
አይዞህ ባይ የሌለው
ታዳጊ የሌለው
ወይ ጠባቂ መልአክ፥ ወይ አበጀ በለው
ደርሶ ከቀንበሩ የማይገላግለው" *
እንኳን ከትላንት ለመናበብ፤ የዛሬውንና የነገውን ራሳችንን ርዕስና ገፅ መች በቅጡ አስቀመጥን! በዚህ ኹሉ ውስጥ ሳይረግፋ የተቀጠፋ፤ ሳይደምቁ ሊታዩ የተጎዘጎዙት እነማን ናቸው? አባቶቻችን እኛን ለመውቀስ ያዩናል ወይስ እኛ ወደ'ነርሱ ዞረን እንወቅሳቸዋለን? ከተማችን(ገላችን ) የሁለታችንም ወዝ፥ ጠረን፥ መልክና መንፈስ ያረፈባት አትመስልም...እርቃኗን ገልበን ብናያት። ለመወቃቀስ የሚያስችል መነሻ የለንም— በእኛና በአባቶቻችን መስመር ስናይ። መንፈሷ መንፈሳችን አይደለም... ቢያንስ የእኔ መንፈስ መዋጮ አይደለም። ሸምስ ተብሪዝ ከአንድ ኢማም ጋ ስለ ባጝዳድ ከተማ እያወሩ የመለሳት መልስ ለልባችን ታደርሰዋለችና እሷን ደግመን
“but no beauty on earth lasts forever. Cities are erected on spiritual columns. Like giant mirrors, they reflect the hearts of their residents. If those hearts darken and lose faith, cities will lose their glamour. It happens, and it happens all the time.” ⁵
ወስብሃት ለኤሊፍ ሸምስ ተብሪዝን ላስታወስሽኝ ብዬ አልፋለሁ። አፈር በሌለበት፥ ምን አይነት አበባ እፈልጋለሁ?
___
₁.መፅሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
₂. ይ.መ.ያ.መ
₃.Tower in the Sky
₄.The Book of Laughter and Forgetting
* በዕውቀቱ ስዩም
₅The forty rules of love
___
📷 RAE New Street Pieces – Hossana, Ethiopia
© Khalid Yohannes