መልካም ዜና !
የቤተክርስቲያን መወረስ ከደርግ ዘመን ጀምሮ የነበረ እስከ አሁንም የዘለቀ ተግባር ነው።አሁን ላይ ከዚህ ቀደም ከህግ ውጭ የተወረሱ የወንጌላውያን ቤተክርስቲያናት ንብረቶች እንዲመለሱ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ወስነዋል። ይህ ውሳኔ እጅግ አስደሳች ውሳኔ ሲሆን የብዙ አባት እና እናቶች የ5 አስርት አመታት የእንባ መልስ ነው።
🎯በዚህም በማያያዝ የቢሾፍቱም ከእግዚአብሄር ዘንድ እንዲደርስ እንፀልይ!
🎯በአዳማም የድሮው የቤተክርስቲያን ንብረት የነበረ አሁን በመንግስት እጅ የአዳሪ ትምህርት ቤት የሆነውንም ከግንዛቤ አስገብተው ለምእመኑ እንዲመልሱም እንጠይቃለን!
🎯ከዚህ ቀደም ሙሉ በሙሉ በመንግስት ከተወረሱት መሀል
1 , የኦሎምፒያ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
2, የኢትዮጵያ ብርሃነ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን (ቡልጋሪያ ያለው የቀድሞ የመጥምቃውያን አዳራሽ)
3, የኢትዮጵያ ወንጌላውዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ (ጉድ ሸፐርድ)
4, የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ አጥቢያ
5, ፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቸርች ይገኙበታል።
እነዚህ ቤተክርስቲያናትና የቤተክርስቲያናት ንብረቶች በቅርብ ይመለሳሉ ብለን እናምናለን። በእነዚህም የእግዚአብሔር ስም የሚነግስ ይሆናል።
ምንጭ : ኤልሻዳይ ቴሌቪዥን
https://t.me/Musiclesson1