ከመረጃ ማሰሻዎች/ browsers/ጋር ተያይዘው ሊፈጠሩ የሚችሉ የመረጃ ምዝበራዎችን እንዴት መከላከል እንችላለን
📌 የበይነ-መረብ አገልግሎትን ለማግኘት በምንፈልግበት ወቅት 1️⃣ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር/ 2️⃣Internet Explorer/ ፣
3️⃣ ሳፋሪ /Safari/ ፣
4️⃣ ክሮም/Chrome/ ፣
5️⃣ ፋየርፎክስ /Firefox/ ወይም 6️⃣ኦፔራ (opera) እንጠቀማለን፡፡ እነዚህ የመረጃ ማሰሻዎች ደግሞ በተጠቃሚዎች ሊደርሱ የሚችሉ የመረጃ ስርቆቶችን እና የመረጃ ጥቃቶችን መከላከል የሚያስችል አማራጮችን ተግብረዋል፡፡
የክሮም ተጠቃሚ ከሆኑ “Advanced Settings;” የፋየርፎክስ “Options” menu; ፣ የኢንተርኔት ኤክስፕሎረር “Internet Options” ፣ የሳፋሪ ተጠቃሚዎች ደግሞ “Preferences” አማራጮችን በመጫን የደህንነት ስርዓታቸውን ማስተካከል ይቻላሉ፡፡ በመሆኑም ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ አሰሳ ለማድረግ ተጠቃሚዎች ሊተገብሯቸው ከሚገቡ የደህንነት አማራጮች ውስጥ፡ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
❶. 'በብሮውዘሮቻችን' ውስጥ የተቀመጡልንን አማራጮች በመከተል የግላዊነት እና የደህንነት ቅንብሮችን ማስተካከል
❷. የኮምፒውተሮቻችን ደህንነት ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ አማራጮችን ተግባራዊ ማድረግ፡፡ ለመረጃ ጥቃት ተጋላጭ የሚያደርጉንን አማራጮች አገልግሎት ማገድ/ Disabling features /
❸. የይለፍ-ቃሎችን በመረጃ ማሰሻችን 'ብሮውዘሮች' ላይ አለማስቀመጥ/ Don’t save passwords/ 'ብሮውዘሮች' ላይ የይለፍ-ቃላትን እንዲቀምጡ መፍቀድ ምቹ ሊሆን ይችላል ግን የደህንነት አደጋዎችን ይፈጥራል፡፡
❹. በ'ብሮውዘሮች' ላይ የምንተገብራቸውን ተሰኪ /plug-ins/ ሶፍትዌሮችን በጥንቃቄ መምረጥ
❺. ብሮውዘሮችን በመደበኛነት ማዘመን፡ የመረጃ ማፈላለጊያዎች እንደ ሌሎች ሶፍትዌሮች ሁሉ መደበኛ ማዘመኛዎች ይቀርቡላቸዋል፡፡ የሚቀርቡ ማዘመኛዎች ለሚፈጠሩ የሶፍትዌር ክፍተቶች መሙያንት ያገለግላሉ፡፡ በመሆኑም ተጠቃሚዎች የሚለቀቁ የደህንነት ማዘመኛዎችን በመደበኛነት መጠቀም ይገባቸዋል፡፡
❻. ለተጠቃሚዎች የሚቀርቡ የደህንነት አማራጮችን ማውረድ እና ማዘመን
እነዚህን 'ብሮውዘሮች' በቤትዎ ወይም በመስሪያቤትዎ አላስፈላጊ አደጋዎችን እንዳይፈጥሩ ለመከላከል ከላይ የተቀመጡ አማራጮቸን ተግባራዊ ማድረግዎን ያረጋግጡ ::
CompuTech