ኢትዮ ቴሌኮም የብሮድባንድ ኢንተርኔት የታሪፍ ቅናሽ ዝርዝርን ይፋ አደረገ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሀይወት ታምሩ ተቋሙ በመደበኛ ብሮድባንድ ማሻሻያ ላይ ሲያደርገው የነበረውን ስራ ማጠናቀቁን አስታውቋል።
ይሄን የብሮድባንድ ኢንተርኔት ማሻሻያ ይፋ ማድረጊያ መርሀ ግብር ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለተሻለ ምርታማነት በሚል መሪ ቃል በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል።
ተቋሙ ማሻሻያውን ማጠናቀቁን አስመልክቶም የብሮድባንድ ኢንተርኔት የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።
በማሻሻያው መሰረትም ለመኖርያ ቤት 69 በመቶ ቅናሽ ፣ ለድርጅቶች 65 በመቶ፣ VPN ደግሞ 72 በመቶ ቅናሽ መደረጉ ተገልጿል።
ለመኖርያ ቤት ለአንድ ሜጋ ባይት ፍጥነት 978 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 499 ብር፣ ለ ሁለት ሜጋ ባይት ፍጥነት 1768 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 699 ብር ፣ ለአራት ሜጋ ባይት ፍጥነት ደግሞ ከ3191 የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 1099 ብር እንዲቀንስ መደረጉ ተገልጿል።
ለድርጅቶች ለአንድ ሜጋ ባይት ፍጥነት 1369 ብር የነበረው ወርሃዊ ክፍያ ወደ 709 ብር፣ ለሁለት ሜጋ ባይት ፍጥነት 2475 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 999 ብር፣ለአራት ሜጋ ባይት ፍጥነት 4468 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 1575 ብር እንዲቀንስ ተደርጓል።
ለድርጅት ደንበኞች የብሮድባንድ ኢንተርኔት ቪ ፒ ኤን ለአንድ ሜጋ ባይት ፍጥነት 1809 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 499 ብር፣ ለሁለት ሜጋ ባይት ፍጥነት 2846 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 899 ብር ለአራት ሜጋ ባይት ፍጥነት 5137 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 1439 ብር እንዲቀንስ ተደርጓል።
ለአዲስ ደንበኞች የብሮድባንድ ኢንትርኔት የአገልግሎት ማስገቢያና የተቀማጭ ገንዘብ (deposit) ሙሉ በሙሉ የተነሳ ሲሆን ለነባር ደንበኞች ደግሞ የተቋረጠ አገልግሎት ማስቀጠያ ከክፍያ ነፃ እንዲሆን ተደርጓል።
ማሻሻያው በዋጋ ብቻ ሳይሆን በፍጥነትም ጭምር መሆኑን ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።
ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም የኢንተርኔት አገልግሎቱ ለመኖርያ ቤት የ 3 በመቶ ፍጥነት ፣ ለ ድርጅቶች 4 በመቶ ፍጥነት ይጨምራል ሲሉ ተናግረዋል።
በመርሀግብሩ ላይ እንደተገለጸው በአንድ ሀገር የ 10 በመቶ የብሮድባንድ ኢንተርኔት እድገት ወይም ስርፀት የ 1 ነጥብ 38 በመቶ አጠቃላይ ምርታማነትና እድገት ያመጣል።
በሔኖክ አስራት
የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም
#መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ።
━━━━━━━━━━━━━━━
📢: @Computer_Android_tricks