⏰መጋቢት 17፣2012⏰
📌ምጥን የዓለም ወሬዎች 📝
#ፊሊፒንስ ውስጥ 9 ዶክተሮች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው መሞታቸው ተሰምቷል። የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ትግል እያደረጉ ያሉት የፊሊፒንስ የጤና ባለሞያዎች በቂ መከላከያ እያገኙ አይደለም ተብሏል።
#ጣልያን ውስጥ በ24 ሰዓት ተጨማሪ 662 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሞተዋል። ከትላንትናው ሪፖርትም መቀነስ አሳይቷል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 8,165 ደርሷል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም 80,539 የደረሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 6,153 ኬዝ በ24 ሰዓት ነው የተመዘገበው።
#የኬንያ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ዛሬ ከሰዓት በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ አንድ 66 ዓመት ኬንያዊ ዜጋ ህይወቱ አልፏል።
#በቻይና በኮሮና ቫይረስ ተይዘዉ ካገገሙ ህሙማን 14 በመቶ የሚሆኑት ድጋሚ ሲመረመሩ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
#ዓለም_አቀፍ ትብብር እና ከ2 እስከ 3 ትሪሊዮን ዶላር። አዎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳለው የኮሮና ወረርሽኝን ለመዋጋት የሚያስፈልጉት እነሱ ናቸው።
የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በሰዉ ዘር ላይ ለመጣው ለዚህ አደጋ የየግል ሩጫ የትም አያደርስም። የአደጉት ሀገራት አዳጊዎችን ቸል አሉ ማለት፣ ቫይረሱ ራሱን ቀይሮና አጠናክሮ እንዲመለስባቸወ ዕድል መስጠት ነው።
#የኒውዮርክ ከተማ #ወረርሽኙ የበረታባት በ24 ሰዓታት ብቻ 285 ሰዎቿን አጥታለች ብለዋል። የምድራችን ሀብታም ከተማ በሆነችው ኒውዮርክ የህክምና ባለሙያዎች ጋዋን አልቆባቸው ቆሻሻ መጣያ ላስቲኮች ለመደረብ ተገደዋል ።
#የኒውዮርክ አገረ ገዢ ግን ማኅበራዊ ርቀት የሆስፒታል አልጋ ፈላጊዎችን ቁጥር እየቀነሰ ነው።ወረርሽኙ ከአሜሪካ አጠቃላይ ሕዝብ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በየቤቱ እንዲከተት አስገድዷል።
#ሩሲያ ሁለት ሚሊዮን ያህል ዜጎቿ ከሰዉ ተነጥለው እንዲሰነብቱ አዘዘች። ሀገሪቱ ትዕዛዙን ያስተላለፈችው ለኮሮናቫይረስ እጅግ ተጋላጭ ናቸው ባለቻቸው ላይ ነው።
#በሩሲያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል ቢባልም፣ ብዙዎች ግን እዉነተኛዉ ቁጥር ከዚያ በብዙ እጅ እንደሚልቅ ይጠረጥራሉ።
#አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ያሽመደመደዉን ኢኮኖሚዋን ለመደጎም የ2.2 ሚሊዮን ዶላር በጀት አፅድቃ ነበር። አዲሱ መረጃ ግን የዛን በጀት በቂነት ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል።
#በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች 1000 ሊደፍን ነው።
ዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (#IMF) እና የዓለም ባንክ ሀብታሞቹ ሀገራት ለአዳጊዎቹ የዕዳ ቅነሳ እና የክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ እንዲያደርጉ ጠየቁ።
የፋይናንስ ድርጅቶቹ የኮሮና ወረርሽኝ በአዳጊ ሀገራት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በድምሩ 60 ቢሊዮን ዶላር መመደባቸውንም ይፋ አድርገዋል።
━━━━━━━━━━━━━━━
📢: @Computer_Android_tricks