🌐 Trading & Investment
📈#Part_2
🖥 ኢንቨስትመንት ምንድን ነው ❓
ባለፈው ፅሁፋችን ስለ Trading introduction በተወሰነ መልኩ ለማየት ሞክረናል ። በዛሬው ፅሁፍ ደግሞ ስለ Investment የተወሰነ ነገር እናያለን :
🏦ሰዎች በፋይናንስ ላይ ስለ ንግድ ወይም ኢንቨስትመንት ሲያወሩ ትሰሙ ይሆናል። ሁለቱም ተመሳሳይ አላማ ቢኖራቸውም የሚከተሏቸው መንገዶች ግን የተለያዩ ናቸው። አንድ ነገር ላይ ኢንቨስት ስታደርጉ ከኢንቨስትመንታችሁ ትርፍ ለማግኘት ነው።
📈ኢንቨስትመንት ማለት ካላችሁ ገንዘብ የሆነ ነገር ላይ በማዋል ተጨማሪ ትርፍ ማግኘት ነው። ለምሳሌ: አንድ ያረጀ ቤት በ1 ሚሊየን ብር ገዝተህ አድሰህ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ4 ሚሊየን ብር ልትሸጠው ትችላለህ።
📊ወይም ደግሞ የሆነ ኩባንያ ላይ Stake/ድርሻ በመግዛት ንግዱ ይበልጥ ሲያድግ ድርሻው የበለጠ ዋጋ እንደሚኖረው በማመን ኢንቨስት ሚያደርጉም አሉ ።
💡ግን ቆይ ትሬደሮች የሚያደርጉት ይሄ አይደለም እንዴ ታድያ ? ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ።
🔍እውነታው ግን ንግድ እና ኢንቨስትመንት ተመሳሳይ አይደሉም ።
💳አዎ አንድ ነጋዴ በአንድ ንግድ ውስጥ አክሲዮኖችን ሊገዛ ይችላል ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው የሚሰሩት። ነጋዴዎች በተደጋጋሚ ወደ ገበያ ገብተው እና ወጥተው በርካታ ትናንሽ ትርፎችን ያገኛሉ።
🪙 ኢንቨስተሮች ግን አብዛኛውን የረጅም ጊዜ አካሄድ ይከተላሉ ካፒታላቸውን በረጅም ጊዜ ውስጥ ትልቅ ትርፍ የሚያስገኙ ፕሮጀክቶች ወይም ንብረቶች ላይ ኢንቨስት ያደርጋሉ።
አጠቃላይ ፋይናንስና ኢኮኖሚ በምን አይነት መልክ እንደሚሄዱ ማወቅ Crypto Space ላይም ስትሰሩ ይጠቅማቿል ።
@Ethiocrypto_433 @Ethiocrypto_433