ክፉ ሰዎች ፣ አጋንንትና ዲያብሎስ በዚህ ዓለም ላይ እንዲኖሩ የተፈቀደላቸው ለምን አንደ ኾነ?
“እነዚህ ኹሉ እንዲኖሩ ለምን እንደ ፈቀደ ብትጠይቅ ፣ ስለማይነገረው የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ቦታ ባትሰጥ ፣ ኹሉንም ነገር እጅግ አጥብቀህ ብትመረምር ፣ ይህንንም ብትዘልቅበት ሌሎች ብዙ ነገሮችን ታጣለህ፡፡
ለምሳሌ ፦ መናፍቃን በዚህ ዓለም ላይ እንዲኖሩ እግዚአብሔር ለምን ፈቀደ ? ለምን ዲያብሎስ እንዲኖር ፈቀደ ? ለምን አጋንንትስ ? ብዙ ሰዎች እንዲሰናከሉ የሚያደርጉ ክፉዎች ሰዎችስ ? ከዚህ ኹሉ በላይም ጌታችን ክርስቶስ እንደ ተናገረ ፥ ቢቻለውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስት ድረስ ኃይል ያለው የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚመጣው ለምንድን ነው? [ማቴ.፳፬፥፳፶]
ስለማይመረመረው የእግዚአብሔር ጥበብ ኹሉን ነገር መተው እንጂ እነዚህን ነገሮች ልትጠይቅ አይገባህም፡፡ አስቀድሞ በእውነትና በጽኑ መሠረት ላይ የቆመ ሰው ብዙ ሞገዶች ቢያላትሙት እንኳን ፣ ስፍር ቍጥር የሌላቸው ማዕበላት ሲነሣሡበት እንኳን አይጎዳም ብቻ ሳይኾን እንዲያውም የበለጠ ብርቱ ይኾናል፡፡
ደካማ ፣ ልፍስፍስና ግድ የለሽ ሰው ግን ምንም መከራ ባይገጥመውም እንኳን አዘውትሮ ይወድቃል፡፡ ምክንያቱ ምን እንደ ኾነ ማወቅ ከፈለግህም በኹላችንም ዘንድ በደንብ የታወቀውን አድምጠው፡፡ በብዙና ልዩ ልዩ በኾነ መንገድ በእኛ ላይ የሚኾነውን እያንዳንዱን ነገር የሚያዝዘው እግዚአብሔር ሌሎች ብዙ ግልፅ የኾኑ ምክንያቶችም አሉትና፡፡
እስከዚያው እኛ የምናውቀው ይህንን ነው ፦ እነዚህ መሰናክሎች እንዲመጡ የፈቀደው ቅዱሳን የሚያገኙት ክብር እንዳይቀንስ ነው ብለናል። እግዚአብሔር ከኢዮብ ጋር ሲነጋገር ግልፅ ያደረገው ይህንን ነው ፦ “ ጽድቅህ እንድትገለጥ እንጂ እኔ በሌላ መንገድ የምፈርድብህ ይመስልሃልን? ” እንዲል። [ኢዮ.፵፥፰]
እንደዚሁም ቅዱስ ጳውሎስ ፦ “በእናንተ ዘንድ የተፈተኑት [የተመሰገኑት የተመረጡት] እንዲገለጡ ፥ በመካከላችሁ መለያየት [ምንፍቅና] ደግሞ ሊኾን [ሊኖር] ግድ ነውና” አለ [፩ኛ ቆሮ.፲፩፥፲፱] “በመካከላችሁ መለያየት [ምንፍቅና] ደግሞ ሊኾን [ሊኖር] ግድ ነውና” የሚለውን በሰማህ ጊዜ ግን ፥ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን የተናገረው እንደ ትእዛዝ ወይም እንደ ሕግ አድርጎ እንደ ኾነ አታስብ፡፡ በጭራሽ አይደለም ! ይልቅ ፥ ሊመጣ ያለውን ነገር ትንቢት እየተናገረና ትጉሃን ከዚያ እንደሚያተርፉ ነው እያመለከተ የነበረው፡፡
“ከዚያም ያልተታለላችሁ የእናንተ ሃይማኖታችሁ ምግባራችሁ ይገለጣል” አለ፡፡"
[#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ]
@deaconchernet