ኦፕን ኤ.ኣይ ጂፒቲ-4o (GPT-4o) የተባለ አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቻት ቦት ሞዴል አስታወዋቀ፡፡
በሞዴሉ ስያሜ ውስጥ የኦ (o) ፊደል ኦምኒ (Omni) የሚለውን የእንግሊዘኛ ቃል የሚያመለክት ሲሆን ይህ ሞዴል ጽሁፍ፣ ድምጽ፣ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ምስሎችን የመረዳት እንዲሁም የመፍጠር አቅምን እንዳሳደገ ተገልጿል፡፡
ይህም በቻትቦት ቴክኖሎጂ ውስጥ ትልቅ እድገት እንደሆነ የተቋሙ ድረ-ገጽ መረጃ ያመለክታል። ጂፒቲ-4o ከዚህ ቀደም ከነበረው ጂፒቲ-4 ቱርቦ ምላሽ በመስጠት አቅሙ ሁለት እጥፍ ፍጥነት ያለው ሲሆን ዕይታዎችንና ድምጽን የመረዳት አቅሙም ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ቴክኖሎጂው በድምጽ ለሚቀርብለት ጥያቄ ፈጣን ምላሾችን በመስጠት እንደ ዲጂታል የግል ረዳት ሆኖ ማገልገል ያስችለዋል፡፡ ሞዴሉ ለድምጽ ጥያቄዎች በ232 ሚሊሴኮንዶች ውስጥ ምላሽ የመስጠት አቅም አለው፡፡ ይህም በሰው ልጆች መካከል የሚደረጉ ተፈጥሯዊ የንግግር መስተጋብሮች ከሚወስዱት 320 ሚሊሴኮንድ ያነሰ ያደርገዋል፡፡
ጂፒቲ-4o ቻት ጂ.ፒ.ቲን ወደ ዲጂታል የግል ረዳትነት በማሳደግ ከሰው ልጆች ጋር ያለውን መስተጋብር ለማሳደግ ዕድል ይዞ ስለመምጣቱ ተነግሯል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
👉 @Desu_tech_tips