የኢትዮጵያ እና የቼክ ሪፐብሊክ 8ኛ የፖለቲካ ምክክር በፕራግ ተካሄደ
****************
የኢትዮጵያ እና የቼክ ሪፐብሊክ ስምንተኛው የፓለቲካ ምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት በቼክ ሪፐብሊክ ፕራግ ተካሂዷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የኢትዮጵያን ልዑክ የመሩ ሲሆን፤ በቼክ ሪፐብሊክ በኩል የሀገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂሪ ኮዛክ ቡድኑን መርተዋል።
በውይይቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር፣ የቼክ ልማት ትብብር ኤጀንሲ እንዲሁም የቼክ ንግድና ኤኮኖሚ ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ በዚሁ ወቅት፤ ቼክ ሪፐብሊክ ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ሀገር መሆኗን አንሰተው፤ ይህን ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀና ሁሉን አቀፍ ትብብር ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያና በቼክ ሪፐብሊክ መካከል የተካሄዱ የከፍተኛ መንግስት ባለሥልጣናት የጉብኝት ልውውጦች መጨመር በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አንዱ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ገለፃ አድርገዋ፤ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለውም የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞች በፈጠሯቸው አመቺ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች የቼክ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ምክትል ሚኒስትር ጂሪ ኮዛክ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክን የጋራ ተጠቃሚነት ያማከሉ በርካታ የትብብር ዕድሎች እንዳሉ ጠቅሰው፤ ሀገራቸው ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁነቷን መግለፃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።