ስነ-ምግባራዊ አመራርን የሚያጎለብት ስልጠና እየተሰጠ ነው
---------
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) የስነ-ምግባር መከታተያ ዋና መምሪያ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመሆን 'ስነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልእኮ ስኬት' በሚል መሪ ቃል ለኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች የተዘጋጀ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ስነ-ምግባርና እና ጸረ -ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፈቃዱ ሰቦቃ ስልጠናው ዘርፍ ተኮርና በተጨባጭ ችግሮች ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ በመሆኑ የጸረ-ሙስና ትግሉን ለማቀጣጠል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።
የኢ.ኮ.ሥ.ኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በውስጥ አቅም ተከታታይ ስልጠናዎችን ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ከፌዴራል ሥነ -ምግባረና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር የሚሰጠው ስልጠና የጸረ ሙስና ትግሉን በተሻለ እውቀትና መረጃ መምራት ያስችላል ብለዋል።
ስልጠናው በቀጣይም በየደረጃው ላሉ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሰራተኞች የሚሰጥ ይሆናል።