Репост из: CryptoTalk-ET 🇪🇹
ትላንት የቢትኮይንን የአንድ ቀን ካንድል መዝጋት ተከትሎ በተለይ በቴክኒካል አናሊስስ ምልከታ በጣም መሰረታዊ እና በመጀመሪያ እርከን ትምህርታዊ ክፍሎች ላይ ያለችውን የዶጂ ካንድል ምልከታ በማየት እና የነበረው ወደላይ የማደግ ሁነት በጣም የተጠናከረ እንደመሆኑ በተጨማሪነትም የፈንዳመንታል አናሊስስ የኢንተረስት ሬት ዜና ቢትኮይን በተወሰነ ደረጃ ወደታች አቅጣጫ ጉዞውን ሊያደርግ እንደሚችል ቅድመግምቴን አስቀምጬላችሁ ነበር። በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱትም በትላንትናው እለት ከነበረው የ105,600 የዋጋ እርከን በመውረድ እስከ 100700 ዶላር ድረስ የወረደበትን ሁነት አሁን ከቅርብ ደቂቃዎች በፊት በወጣው ዜና ጋር አቆራኝቶ ሊነካ የቻለበት ሁነትን ልንመለከት ችለናል። ከዚህ ልንረዳ የምንችለው በተለይ በአነስተኛ ታይም ፍሬም ላይ የምትገበያዩ ቤተሰቦች አንዴ የገበያውን አካሄድ ከፍ ባሉ የግብይት ታይም ፍሬሞች ከተመለከታችሁ በኋላ በመሀል የሚገኙትን የመግዛት የመሸጥ እድሎች በጥንቃቄ መጠቀም እንደሚቻላችሁ ነው። ተጨማሪ የክሪፕቶ እንቅስቃሴዎችን አንዴ የቢትኮይን ሁነት እና እንቅስቃሴ ከለየለት በኋላ መጠቆም የምጀምር ሲሆን በተለይ አብዛኛዎቻችሁን ካላስፈላጊ ኪሳራዎች ለመጠበቅ ስል የማደረግው ጥንቃቄ በመሆኑ በትእግስት ትጠባበቁኝ ዘንድም ለመጠቆም እወዳለው። መልካም ምሽት።