ሐሜተኛ ሰው የእግዚአብሔር ጠላቱ ነው። በጠላትህ ውድቀትና ሞት ደስ አይበልህ፤ ባዘኑት ላይ አትሣለቅ፤ ለዕውሩ መሰናክል አታኑርበት። ስትጸልይ ለመቀመጥ አትቸኩል፤ ለጸሎት ጽሙድ ኾነህ በቆምክበት ቦታ ኹሉ አትነቃነቅ፤ በመካነ ጸሎትህ ላይ አዘውትረህ ቆመህ ተገኝ። ለለመነህ ኹሉ ስጥ፤ ከሌለህ ደግሞ እግዚአብሔር ይስጥህ ካለው ያድርስህ ብለህ በለዘበ ቃል ተናገር። የምትሠራውን ሥራ ኹሉ ፊት አይተህ አድልተህ አትሥራ። የደረሰብህን ኹሉ እግዚአብሔርን አመስግነህ ተቀበል። ይህንን ያደረግህ እንደ ኾነ በእግዚአብሔር ትእዛዛትና ሕግጋት አንተ በእውነት ፍጹም ነህ። እኔስ በእውነት የእግዚአብሔርን ጥበብ አደንቃለሁ።
❝በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን።❞
—1ኛ ቆሮንቶስ 15: 19
©️ መምህር ዲ/ን እስጢፋኖስ ደሳለኝ
❝በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን።❞
—1ኛ ቆሮንቶስ 15: 19
©️ መምህር ዲ/ን እስጢፋኖስ ደሳለኝ