መላ ዐረቢያን የሚያስተዳድረው የኢስላማዊ ስረወ መንግስቱ መሪ ዑመር ረዐ የመስጂደል ሀራምን ግቢ ለማስፋፋት የዐባስ ቤት እንዲፈርስ እና ለዐባስም በምትኩ ቆንጆ ቤት ሌላ ቦታ እንዲገነባለት ትዕዛዝ አስተላለፈ።
አባስም፦‹‹ቤቴ እንዲፈርስ እልፈቅድም›› አሉ።
(መብት)
ዑመርም፦‹‹ዐባስ! የአላህን ቤት ቤት ለማስፋፋት እኮ ነው›› አለው።
(ማባበል)
ዐባስም፦‹‹አልፈቅድም አልኩኝ እኮ ዑመር!›› ብሎ መለሰ።
(መሪ ፊት መብትን ማስከበር)
ዑመርም፦‹‹እንግዲያውስ ወደ ሸንጎ ሂደን እንዳኝ፤ ሚዳኘንን ዳኛም አንተው ምረጥ›› አለው።
(ፍትህ እና መተናነስ)
ዐባስም፦‹‹ዳኛ ሹረይሕ ይዳኘን›› አለ።
(ጥሩ ስም ሲኖር)
ዑመርም፦‹‹ተስማምቻለሁ››አለ።
(መተናነስ)
ዐባስም፦‹‹የምእመናን መሪ ሆይ! በል ዳኛ ሹረይሕን ጥራው'ና ይዳኘን›› አለ።
ዑመርም፦‹‹ዳኛ ወደሚዳኛቸው ሰዎች አይሄድም፤ እነሱ ናቸው ወደ እሱ መሄድ ያለባቸው። ተነስ እኛ እንሂድ›› አለው።
(መርህ)
ሁለቱም ተያይዘው ወደ ሸንጎው ዳኛ አመሩ። ሸንጎው ፊት ሲቆሙም ዳኛው፦‹‹የምእመናን መሪ...›› ብሎ ዑመርን ሲጠራ ዑመርም፦‹‹ዑመር ብለህ ጥራኝ፤ ሸንጎ ላይ እስካለሁ ድረስ›› አለው።
(የሸንጎ እና የዳኛ ክብር)
ሸንጎው ተጀመረ። ሁለቱም ስሞታቸውን ለዳኛው ካሳሰቡ በኋላ ዳኛው እንዲህ ስል ውሳኔ አስተላለፈ፦‹‹ከሀራም የፀዳ ቦታ ማለት መስጅድ ነው።መስጂድን ለማስፋፋት ያለ በጎ ፈቃዱ የዐባስን ቤትም ማፍረስ ደግሞ ሀራም ነው››
(ፍትህ ፣ ሀላፊነት፣ ድፍረት)
ዑመርም ክሱ ውድቅ ሲሆንበት፦‹‹ምንኛ ፍትሀዊ ዳኛ ነህ! ሸንጎህ ያማረ›› አለው።
(ዕውነታን መቀበል)
ዑመር እዝያው ሽንጎ ላይ ሁኖ ይህንን ዳኛ የዳኞች ሁሉ የበላይ አድርጎትም ሾመው።
(ዕምነት)
ይህን የተመለከተው ዐባስም፦‹‹እንግዲያ ነገሩ እንዲህ ተሆነማ ፤ እኔም ቤቴን በገዛ ፈቃዴ ለአላህ ብዬ ለቅቄያለሁ›› አለ
ምንጭ፦
البدايه والنهايه