የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ
ጅማ፤ ታኅሣሥ 12/2017 ዓ.ም (ኢ.መ.ብ.ባ)
ባለሥልጣኑ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተውጣጡ ሰልጣኞችበጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከል፣ በመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆዎች፣ በሃቅ ማጣሪያ መንገዶች እና በሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ዙሪያ በጅማ ከተማ ነፃ ሰልጠና ሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የአቅም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ ቦጋለ ተድላ፤ በመሰረታዊ ጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆዎች፣ በሃቅ ማጣሪያ መንገዶች ላይ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ እና ኃላፊነትን የተላበሰ የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት በማዳበር በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ራሳቸዉን ብሎም ሀገራቸዉን ከተዛቡ መረጃዎች እንዲጠብቁ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡
አስተያየታቸውን የሰጡን ሰልጣኞች በበኩላቸው፤ በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ መልዕክቶች ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገባቸው የጥቅማቸውን ያህል ጉዳታቸው የከፋ መሆኑን ከስልጠናው ተገንዝበናል ብለዋል። አያይዘውም፤ በአሁኑ ወቅት የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት እያደረሰ ያለው ጥፋት አደገኛ በመሆኑ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃዎችን ሲመለከቱ በ#9192 ነጻ የስልክ መስመር ደውለው በመጠቆም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ስልጠናዉን ለተካፈሉ ሰልጣኞች ስርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡