በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ስፍራዎች ወጣቶች እየታፈሱ ወደ ወታደራዊ ካምፖች እየተላኩ መሆኑ ታውቋል።
ይህ ድርጊት እየተፈፀመባቸው ያሉት በተለይ በጉልበት ስራ የሚተዳደሩ የደቡብ ልጆች ላይ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመው ባሳለፍነው ሁለት ሳምንት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩት ተይዘው ተወስደዋል ብለዋል።
የሸክም ስራ የሚሰሩትን እነዚህ ልጆችን አፍሰው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱ በኋላ የተወሰነ ግዜ በእስር አቆይተው ወደ ወታደራዊ ካምፕ እንደሚወስዷቸው ምንጮቻችን ነግረውናል።
ባሳለፍነው ሳምንት ይህ ድርጊት ሲፈፀምበት የነበረው ቦታ ኮዬ ኮንዶሚኒየም አዲስ ከተማ ፖሮጀክት 16 የሚባለው አካባቢ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።
"ወዴሳ ወረዳ አንድ ጣብያ አለ፣ በፊት የአዲስ አበባ ፖሊስ ነበር፣ አሁን ሸገር ከተማ ከሆነ በኋላ የኦሮሚያ ሚሊሺሻ ነው ያለበት" ያሉን አንድ የመንግስት ምንጫችን ለእያንዳንዱ ሚሊሺያ ኮታ እየተሰጠ ወጣቶችን አፍሰው እንዲያመጡ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ሌላኛው ምንጫችን ደግሞ የዚህን የአፈሳ ድርጊት መኖር አረጋግጦ በተለይ በሸገር ከተማ በጠራራ ፀሀይ እየተፈፀመ መሆኑን ተናግሯል።