Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ከታች የዚህን ሌባ ጉድ ተመልከቱ
በ1.8 ቢልየን ብር ከቦታቸው ሳይፈናቀሉ ቤት ይሰራላችኋል ተብለው የነበሩት የለገሀር ኤግል ሂልስ ፕሮጀክት ሳይት ነዋሪዎች በሶስት ቀን ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ተነገራቸው።
(መሠረት ሚድያ)- ከስድስት አመት በፊት የለገሀር ኤግል ሂልስ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ሲጣል በ1.8 ቢልዮን ብር የመኖርያ ቤት ተገንብቶላቸው እዛው እንደሚኖሩ ተነግሯቸው የነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎች በሶስት ቀን ውስጥ እቃቸው አውጥተው የካዛንችስ ነዋሪዎች ወደሄዱበት ቦታ እንዲሄዱ እንደተነገራቸው ገለፁ።
"ዶ/ር አብይ የመሰረት ድንጋይ ሲያስቀምጡ ባደረጉት ንግግር በአካባቢው ላይ እየኖሩ ለሚገኙ 1,650 አባወራዎች እዛው ፕሮጀክቱ አካባቢ ሰርተን በዘመናዊ ቤት ኑሮ እንዲኖሩ እናደርጋለን፣ ለዚህም የኤግል ሒልስ ባለቤቶች 1.8 ቢልየን ብር ሰጥተውናል ብለው ተናግረው ነበር" የሚሉት ነዋሪዎች አሁን አዲስ ዱብዳ የሆነ መረጃ ተነግሮናል ብለዋል (ለንግግሩ ቪድዮውን ይመልከቱ)።
ባሳለፍነው ቅዳሜ ጥቅምት 23/2017 ዓ/ም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 የመሬት አስተዳደር ኃላፊዎች የተወሰኑ ነዋሪዎችን ሰብስበው በሶስት ቀናት ውስጥ እጣ አውጥታችሁ የካሳንችስ ነዋሪዎች የሔዱበት አካባቢ ትገባላችሁ፣ ተዘጋጁ ብለው ለነዋሪው ማስጠንቀቂያ ሰጥተው እንደሄዱ ለመሠረት ሚድያ የደረሰው ጥቆማ ያሳያል።
"ነዋሪው በጣም ተደናግጧል፣ እስቲ ብትዘግቡልን እና ህዝብ ቢያውቅልን ስንል አደራ እንላለን" ያሉት ነዋሪዎች ተስፋ አድርገው ለአመታት ቢጠብቁም ቃል ታጥፎ ከከተማ ውጭ እንዲሄዱ መደረጋቸው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።
ይህ ከአልሚው ኢግል ለተነሺዎች ቤት መገንቢያ ተብሎ ተሰጥቶ የነበረው 1.8 ቢልዮን ብር የት እንደደረሰ በመንግስት የተባለ ነገር የለም።