የአዲስአበባ ማህበራዊ ንቅናቄ(አማን) እና አራዳ ተዋሀዱ!
ሁለቱ አዲስአበባ ላይ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አደረጃጀቶች ተዋህደዋል። ሁለቱ አደረጃጀቶች ለየብቻ እንዲሁም በጥምረት ላለፈዉ አንድ አመት ገደማ በከተማችን በአዲስአበባ ላይ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል። እንደማሳያ በተለያዩ የከተማዋ ጎዳናዎች ላይ የተቃውሞ በራሪ ወረቀቶችን መበተን, ባነሮችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ በመስቀል እንዲሁም፤ የገዥዉ ብልፅግና ቢሮዎች ላይ የማስጠንቀቂያ ፍንዳታዎችን በመፈፀም ያለፈዉን አንድ አመት ገደማ አሳልፈዋል።
ሆኖም ግን የአላማም ሆነ የግብ ልዩነት ባለመኖሩ እንዲሁም አዲስአበባ ላይ ያሉ የተበጣጠሱ ትግሎን ወደ አንድ አምጥቶ ጠንካራ የማህበራዊ ንቅናቄ ድርጅት መመስረት እንዳለበት በመታመኑ በሁለቱ ንቅናቄዎች በተደረጉ ሰፋ ያሉ ውይይቶች ወደ አንድ "አማንአራዳ" የተባለ የማህበራዊ ንቅናቄ ድርጅትነት እንዲመጡ ተደርጓል።
ሁለቱ ንቅናቄዎች ከተዋሀዱበት ጊዜ አንስቶ ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅርን ከመመስረት ጀምሮ በተለያዩ የአዲስአበባ ሰፈሮች መዋቅሮችን በመዘርጋት, ግብ እና አላማችውን በማጥራት የማህበራዊ ንቅናቄ እቅዶችን እንዲሁም የትግል ማንፌስቶን ከማውጣት ጎን ለጎንም የተለያዩ ስልጠናዎችን በመዉሰድ ድርጅታዊ ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል።
በመሆኑም ለመላዉ የአዲስአበባ ህዝብ እና አገዛዙን መታገል የሚፈልጉ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ከአማንአራዳ ጋር በአጋርነት እንትቆሙ የትግል ጥሪ እናስተላልፍለን።
አማንአራዳ ማህበራዊ ንቅናቄ
ጥር/2017