🧒 ህፃናቶች በዚህ ወቅት ከፍተኛ የአምዕሮ ጫና ውስጥ እንዳይገቡ ምን መደረግ አለበት?
👧
ልጆች በሚጨነቁ ሰዓት የተለያየ የባህሪ ለውጦች ያሳያሉ። ወደ ወላጆች መጠጋት / መጣበቅ ፣ በቀላሉ መደንገጥና መበሳጨት ፣ አልጋቸው ላይ ሽንት መሽናት የመሳሰሉት ሲሆን የልጆቻችንን ሁኔታ በመመልከት አስፈላጊውን ክብካቤና ፍቅር መስጠት ያስፈልጋል።
🧓
በዚህ አይነት ከባድ ወቅት ህፃናቶች የወላጆቻቸውን ፍቅር እና ትኩረት ይሻሉ። ስለዚህ ተጨማሪ ትኩረትና ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል። በደንብ ልናዳምጣቸው ፣ በተረጋጋ መንፈስ ልናናግራቸውና ልናረጋጋቸው ያስፈልጋል።
👩
ሁልጊዜ ልናቀርባቸውና ካጠገባችን እንዳይለዩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለብን። ከእኛ በሚርቁ ሰዓት (ሆስፒታል ታመው ቢተኙ) በስልክ እና በመገናኛ መንገዶች አብሮነታችንን ልናሳያቸው ይገባል።
👳♀️
የቀኑን ዕቅድ በማውጣት በዚያ እንዲመሩ መርዳት ያስፈልጋል። አዳዲስ የፈጠራ መንገዶችን በመጠቀም ትምህርታቸውን የሚቀጥሉበት ፣ የሚጫወቱና የሚዝናኑበት ሁኔታ መፍጠር ይቻላል።
🧕
በአለም ዙሪያ ስላለው ሁኔታ ማስተማር ፣ ራሳቸውን ከቫይረሱ የሚጠብቁበትን መንገዶች እድሜአቸውን ባገናዘበ መንገድ ማሳየት ፣ በተጨማሪም ቤተሰብ ቢታመም እንዲሻለው ሆስፒታል ገብቶ ሊታከም እንደሚችል ማስረዳት ያስፈልጋል።
👱♂️
ብዙ ሰዓት ስለ ወረርሽኙ ብቻ የሚያወሩ የሚዲያ አውታሮችን ህፃናት ባሉበት አለመክፈት።
Translation from: © "Helping children cope with stress during COVID-19."
Yared Agidew (MD)
@EthioBini_bot @EthioBini