የከፍተኛ ተስፋ - ጥቅምና ጉዳት
===================
ተስፋ ከሁለት ነገሮች የተዋቀረ ስሜት ነው - ፍላጎትና የፈለጉት ነገር የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነው የሚል አሰተሳሰብ። አርስቶትል "ተስፋ ቆሞ የሚሄድ ሰው ህልም ነው።" ይላል። ተስፋ የስጋት ፍፁም ተቃራኒ ስሜት ይሁን እንጂ በእያንዳንዱ ተስፋ ስር የተደበቀ ስጋት እንዲሁም በእያንዳንዱ ስጋት ስር የተሸሸገ ተስፋ አለ። ህይወት ያለ ተስፋ ህይወት አይሆንም።
ተስፋ በአስቸጋሪ ጊዜያት ትእግስት እና ወኔ ይሰጣል። ይሁን እንጂ ምክኒያታዊ ያልሆነ ተስፋ ስቃያችንን ያረዝመዋል። አንዳንዴም አስተሳሰባችንን ያዛባዋል። ሁኔታዎችን ስንመረምር በፍላጎታችን፣ በምኞታችን እና በተስፋችን ተመስርተን ሳይሆን በነባራዊው እውነታ ላይ መሆን አለበት። ሎተሪ ቢደርሰን ብለን ልንመኝ እንችላለን። የፈለገ ብንመኝ የመድረስ እድሉ ከዜሮ አጠገብ እንደሆነ መርሳት የለብንም። አንዳንድ ሰዎች ግን ከመጓጓትና ተስፋ ከማድረግ ብዛት የሚደርሳቸው የሚደርሳቸው ይመስላቸዋል።
ተስፋ የምናደርገው ነገር መጠኑ ከፍ ሲል ባይሳካ የመናደድና የማዘን እድላችን አብሮ ይላል።
....ከፍ ከፍ፣ ከፍ ከፍ
ከፍ ከፍ፣ ከፍ ከፍ፤
ኃላ የወደቅህ እለት
አጥንትህ እንዳይተርፍ።...... እንደተባለው።
ከፍተኛ ተስፋ ሰዎች ማድረግ የሚገባቸውን እንዳያደርጉ ምክኒያት የሚሆንበት ጊዜ አለ። ተስፋ እንደሚያስፈልግ አያጠያይቅም። ከልክ ያለፈ ተስፋ ግን ጉዳቱ ያመዝናል።
ግለሰቦች ርቀታችንን እንደምንጠብቅ፣ በጣም አስፈላጊ ካልሆነ ከቤት እንደማንወጣ፣ እጃችንን እንደምንታጠብ ተስፋ አደርጋለሁ።
ጤና ሚኒስተር አስፈላጊውን ህክምና፣ ቅኝትና ልየታ እንዲሁም ለባለሞያዎች ራስን የመጠበቂያ እቃዎች በቁርጠኝነትና በፍጥነት እንዲዳረስ እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ።
መልካም ጊዜ!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው (የአእምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት)
@EthioBini_bot @EthioBini