ባይፖላር ዲስኦርደር (bipolar disorder)
ባይፖላር ዲስኦርደር በሁለት ተቃራኒ ስሜቶች ማለትም በደስተኝነትና በድብርት መፈራረቅ የሚገለጽ ሲሆን በዚህ ችግር የተጠቃ ሰው ጊዜ እየጠበቀ በደስታና በድብርት ፅንፍ ውስጥ ይመላለሳል፡፡ ይህ ችግር በወጣትነት ወይም በጎልማስነት እድሜ መጀመሪያ ላይ የሚከሰት ሲሆን እድሜ ልክ የሚቆይ ህመም ነው፡፡ በዘር የመተላለፍ እድሉም ከፍተኛ ነው፡፡
ምልክቶች
ባይፖላር ዲስኦርደር በውስጡ የማንያ (ደስተኝነት፣ ቁጡነት/ ብስጩነት) እና የዲፕረሽን (ድብርት) ኡደቶችን እንደመያዙ መጠን ...
ማንያ ምእራፍ ላይ ሳሉ የሚታዪ ምልክቶች፡-
• ፋታ አልባ እንቅስቃሴና ጉልበተኝነት
• ቅብጥብጠኝነት፣ በሀሳብ መጋለብና በንግግር መንቀዥቀዥ
• እጅግ አብዝቶ መጨነቅ
• ያለምክንያት የመፈንጠዝና ግራ የሚያጋባ የደስተኝነት ስሜት
• የበዛ የጉራና በራስ የመተማመን ስሜት
• እንቅልፍ ማጣት
• የወሲብ ስሜት መጨመር
በድብርት ምእራፍ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ የሚታዪ ምልክቶች
• የበዛ/የማያቋርጥ የሀዘን፣ የመረበሽና የባዶነት ስሜት
• ተስፋ መቁረጥና ጨለምተኝነት
• በፊት በሚደሰቱባቸውና በማንኛውም ነገርች ላይ ፍላጎት ማጣት
• ትኩረት ማጣት
• ክብደት ማጨመር/መቀነስ
• እንቅልፍ መብዛት/ማነስ
• ራስን ለማጥፋት ማሰብ
እነዚህን ምልክቶች የሚያሳዪ ሰዎች ወደ ህክምና ቦታ ሄደው እርዳታ ማግኘት አለባቸው፡፡ ይህን ችግር ለማከም የሚታዘዙ የተለያዩ መድሀኒቶች ሲኖሩ በተጓዳኝ የሚሰጥ የማማከር አገልግሎትም ህሙማንን ወደ ቀድሞ ጤናቸው ለመመለስ ይረዳል፡፡
@EthioBini @EthioBini