ሜሲ ባለመኖሩ ደጋፊዎች ይቅርታ ተጠየቁ !
የአሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ ዛሬ ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ወደ ቴክሳስ በማምራት ከሂውስተን ጋር የሜጀር ሊግ ሶከር ጨዋታውን ያደርጋል።
አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በአሰልጣኙ እረፍት የተሰጠው መሆኑን ተከትሎ በጨዋታው አይሳተፍም።
ይህንንም ተከትሎ የኢንተር ሚያሚ ተጋጣሚ ቡድን ሂውስተን ሊዮኔል ሜሲ ይሳተፋል ብለው ጨዋታውን ለመታደም ትኬት የቆረጡ ደጋፊዎቹን ይቅርታ ጠይቋል።
የክለቡ ደጋፊዎች የሊዮኔል ሜሲን ወደ ስፍራው አለማቅናት ዜና ሲሰሙ በመሳጨታቸው ተነግሯል።
ስለ ተጋጣሚ ቡድን አሰላለፍ መወሰን አንችልም ያለው ክለቡ በመግለጫው ደጋፊዎቹ ለማካካሻ እንዲሆናቸውም ነፃ ትኬት ማቅረቡን ገልጿል።
ሊዮኔል ሜሲ የለም ብለው ሳይቀሩ የምሽቱን ጨዋታ የሚታደሙ ደጋፊዎች በትኬቱ የወደፊት ጨዋታ በነፃ እንዲመለከቱ መወሰኑን ክለቡ አሳውቋል።