ግብፅ እየከፈለቻቸው ፀረ ኢትዮጵያ አቋም ሲያራምዱ የነበሩት ሴናተር በ15 ዓመት እስር እንዲቀጡ ተጠየቀ
------
የግብጽን ጥቅም ለማስከበር ጉቦ ተቀብለዋል የተባሉት አሜሪካዊው ሴናተር በ15 ዓመት እስር እንዲቀጡ ተጠየቀ፡፡
በሴናተርነታቸው ያገኙትን የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢነት ስልጣን ተጠቅመው በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያን ለመጣል ሲሰሩ እንደነበር ይታወሳል።
በፈረንጆቹ 2020 ላይ የወቅቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጫና አድርገዋል ተብሏል፡፡
እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ከሆነ ፖለቲከኛው ይህን ያደረጉት ከግብጽ ባለስልጣናት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ጉቦ ከተቀበሉ በኋላ ነበር፡፡
ሜንዴዝ ከግብጽ እና ኳታር ኩባንያዎች ጋር ያልተገባ ጥቅም ትስስር በመፍጠር 150 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ወርቅ እና ከ450 ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ ተከፍሏቸዋል የተባለ ሲሆን፤ የሀገሪቱ ፍትህ ተቋማት ባደረጉት ምርመራ ሜኔንዴዝ በጉቦ መቀበል፣ በፍትህ ማዛባት እና ሌሎችም ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡
ሜኔንዴዝ ከተደረገባቸው የወንጀል ምርመራ በኋላ ካሳከፍነው ነሀሴ ወር ጀምሮ ከሀገሪቱ ምክር ቤት አባልነት እና ከውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነታቸው ታግደው ቆይተዋል፡፡
በኒው ጀርሲ በተካሄደ ችሎት ቦብ ሜኔንዴዝ በፈጸሙት የሙስና እና ፍትህ ማዛባት ወንጀል የ15 ዓመት እስር እንዲተላለፍባቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም በ71 ዓመቱ ፖለቲከኛ ቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የመጨረሻ ብይን ለማስተላለፍ ለጥር 21 ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡