በሶማሊያ በሚገኘው የአይሲስ ክንፍ ላይ የሚካሄደው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል
------------
ለአንድ ወር ያህል የፑንትላንድ የፀጥታ ኅይሎች በእስላማዊ መንግሥት ተዋጊዎች መደበቂያ ምሽጎች ላይ እርምጃቸውን አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን፣ በቅርቡ ቱርማሳሌ በተሰኘው ቁልፍ ሥፍራ የተደረገው ከባድ ግጭት ተጠቃሽ ነው።
በሁለቱም ወገኖች ላይ ጉዳት ቢደርስም፣ የፑንትላንድ ኅይሎች በርካታ ሥፍራዎችን በመቆጣጠር የበላይነት አግኝተዋል ተብሏል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ባለፈው ቅዳሜ በሶማሊያ በሚገኙ አንድ ከፍተኛ የእስላማዊ መንግሥት ጥቃት አቀናባሪና በሌሎቹም የቡድኑ ዓባላት ላይ ወታደራዊ የአየር ጥቃት እንዲፈፀም አዘዋል።
የአየር ጥቃቶቹ በጎሊስ ተራራማ ቦታዎች ላይ መደረጋቸውንና በሲቪሎች ላይ ጉዳት እንዳልደረሰም የአሜሪካው የመከላከያ ምኒስትር ፒት ሄግሴት አስታውቀዋል።
የሮይተርስ ዜና ወኪል ዝርዝር ጉዳዮችን በተመለከተ ከገለልተኛ ወገኖች ማረጋገጥ እንዳልቻለ አስታውቋል።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉና በሶማሊያ ፕሬዝደንታዊ ጽ/ቤት የሚገኙ አንድ ባለሥልጣን የአየር ጥቃቶቹ መፈፀማቸውን አረጋግጠው፣ የሶማሊያ መንግሥት እርምጃውን በመልካም እንደሚቀበለው አስታውቀዋል።
አሜሪካ ለበርካታ ዓመታት በሪፐብሊካኑም ሆነ በዲሞክራቶቹ የአስተዳደር ዘመኖች ሶማሊያ ውስጥ የአየር ጥቃት ስትፈፅም ቆይታለች፡፡