ፍልስጥኤማዉያን ጋዛን እንዲለቁ የሚያስችል ዕቅድ እንዲነድፍ ታዘዘ
-----------
ትዕዛዙ የተላለፈው በእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ነው።
የሚንስትሩ ትዕዛዝ የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥን ለመቆጣጠር እንደሚፈልጉ ካስታወቁ በኋላ ዓለማቀፍ ተቃዉሞ እየተሰማ ባለበት ወቅት ነው።
የመከላከያ ሚንስትሩ እስራኤል ካትዝ፣ ትራምፕ ከ2 ሚሊዮን በላይ ፍልስጥኤማዉያን የሚኖሩባትን ጋዛን ለመቆጣጠር ማቀዳቸውን አድንቀዋል።
"የፕሬዚደንቱን በድፍረት የተሞላ ዕቅድ በደስታ እንቀበላለን ፤ በየትኛውም ዓለም እንደሚሆነው የጋዛ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸዉ በነጻነት መውጣት እና መሰደድ ሊፈቀድላቸው ይገባል » ብለዋል።
ሚንስትሩ ፍልስጥኤማዉያኑ በየብስ ፣ በባህር አለያም በአየር እንደምርጫቸው ከጋዛ መውጣት እንዲችሉ አማራጮች ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
የአረብ እና የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራትን ጨምሮ በርካታ ሃገራት የፍልስጥኤማዉያኑን ከሃገራቸው እንዲሰደዱ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ሃሳብ ተቃዉመዋል።
የፍልስጥኤም አስተዳደር ፕሬዚዳንት መሐሙድ አባስ በበኩላቸው የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዕቅድ በይፋ ውድቅ ባደረጉበት መግለጫቸው ።
" ህጋዊ የፍልስጥኤማዉያን መብቶች ለድርድር አይቀርቡም" … ሃሳቡም " ከባድ የመብት ጥሰት ነው " ብለውታል።
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ በበኩላቸው“የፍልስጤም ሕዝብ በገዛ ምድራቸው እንደሰው የመኖር የማይገሰስ መብቶች» እንዳላቸው አጽንዖት ሰጥተዋል።