በክፍል ሁለት ጽሁፋችን የኢየሱሳዊያንን (jesuits) ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተከትሎ ህዝቡ የቆየ ሃይማኖቱን በሮም ካቶሊክ እምነት ላለመቀየር ያደረገውን ተቃውሞ ተመልክተን ነበር። ኢየሱሳዊያኑም ቢሆኑ የራሳቻውን ሃይማኖት በአገሬው ህዝብ ላይ ለመጫን ያደርጉ የነበረውን ጥረት ያክል የህዝቡን ኑሮ ከመሰረቱ ለመቀየር የሚረዱ የፈጠራና የለውጥ ትምህርቶችን ለማስተማር ያደረጉት ጥረት እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም። በፖርቱጋሎች የተጻፉት የታሪክ መዛግብት በግልጽ እንደሚያሳዩት ኢየሱሳዊያኑ ሚሲዮኖች ትልቁ ትኩረታቸው የነበሩት ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ነበሩ። ቅዳሜና እሁድን እንደ ሰንበት ተቀብሎ ያከብር የነበረውን የረጅም ዘመን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ እሁድን ብቻ ሰንበት እንዲያከብር፣ ካህናቱ ሳያገቡ በድንግልና እንዲኖሩ ከማስተማር ባሻገር ሰለ ተሻሻለ የግብርና ዘዴ፣ ስለዘመናዊ የከብት እርባታ፣ስለ ደን ጥበቃ ዘዴ እና ስለ ዘመናዊ ገበያና መገበያያ አገሬውን ለማስተማር ፍላጎት አልነበራቸውም።
የጣናዋ ጀልባ
አንድ ፖርቱጋላዊ ከእንጨት የተጠረበ ጀልባ ሰርቶ በጣና ሀይቅ ላይ ይቀዝፍ ነበር። ይሁንና ኋላቀር በሆነ መንገድ ጀልባዎችን ሰርተው ይጠቀሙ የነበሩ የዘመኑ ሰዎች ይህን ዓይነቱን የቴክኖሎጂ ሽግግር ተከትለው የተሻሻለ ጀልባ ሰርተው ሲጠቀሙ አናስተውልም።
በሌላውም ዘርፍ ያየን እንደሆነ ሚሲዮናዊያኑ የራሳቸውን መኖሪያ በዘመናዊ መልክ በግንብ ይገነቡ የነበረ ሲሆን ፣ የአገሬው ህዝብ ግን ኑሮው እዛችው የሳር ጎጆ ውስጥ ነበር። ኢትዮጵያ ውስጥ በዘመኑ የነበሩት ኋላ ቀር የእርሻ መሳሪያ፣ የዲንጋይ ወፍጮ፣ የእንጨት ትራስ ዛሬም ድረስ በአንዳንድ አከባቢ በጥቅም ላይ ሲውሉ ማየት አገሪቱን የኢትኖሎጂካል ሙዚየም ያስመስላታል።
ፖርቱጋሎች እና ፖርቱጋሎቹ ከህንድ ያስመጧቸው ባለሞያዎች ጥለው ያለፏቸው ጥቂት የቴክኖሎጂ አሻራዎች ግን አልታጡም። ከነዚህም መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ግንባታ ነው። ፖርቱጋሎች የገነቧቸው ቤተ-መንግሥቶች ፣ ድልድዮችና ቤቶች ዛሬም ድረስ በአንዳንድ ቦታ አሻራቸው አልጠፋም።
ዘመነ ጎንደር
የጎንደር ከተማ በ1636 ዓ.ም. መቆርቆር የፈጠራና ለውጥ እንቅስቃሴን ያነቃቃ ክስተት ነበር። በዘመኑ የተገነቡት የፋሲለደስና የሌሎቹም ነገሥታት ቤተ-መንግሥት የአዲስ ዘመን ጅማሮ ምልክቶች ነበሩ። የታዋቂው ተጓዥ ጀምስ ብሩስ ዘገባ ይህንን ሀሳብ የሚያጠናክር ሆኖ እናገኘዋለን። እንደ ጀምስ ብሩስ ዘገባ አጼ ኢያሱ ዳግማዊ ቤተመንግሥቱን ለማስጌጥና ለማስዋብ የግሪኮቹን እውቀትና ጥበብ በሚገባ ከመጠቀሙም ባሻገር እራሱ አጼ ኢያሱ ዳግማዊ በራሱ እጅ የግሪኮቹን መሳሪያዎች ተጠቅሞ የተለያዩ ሙከራዎችን ያደርግ ነበር። ለዚህም እንደምሳሌ ለመጥቀስ ኮምፓስ በመጠቀም ልክ እንደ ግሪኮቹ ሁሉ የኮከብ ምልክትን መሳል ችሎ ነበር።
አጼ ኢያሱ ቀዳማዊም እንዲሁ ለፈጠራና ለውጥ ትልቅ ፍላጎት የነበረው ንጉሥ ነበር። በካይሮ የፈረንሳይ ቆንጽል የነበረው De Maillet እንደጻፈለን ኢያሱ ቀዳማዊ ከካይሮ የተለያዩ ባለሞያዎች (ግንበኞች፣አናጺዎች፣አርክቴክቶች፣ የህክምና ባለሞያዎች፣ወዘተ) እንዲመጡለት ደብዳቤ ይለዋወጥ ነበር። ሌላው ምስክር ፈረንሳዊው ተጓዥ Charles Poncet በጻፈው ማስታወሻ እንደገለጸው አጼ ኢያሱ ወደ ጎንደር የመጡላቸውን መድኃኒቶች ምንነትና አጠቃቀማቸውንም ጭምር እየጠየቁ በጽሁፍ እንዲቀመጥ ያደርጉ ነበር። ከዚህም ባሻገር ንጉሡ የመድኃኒት አዋቂ አውሮፓዊያንን መድኃኒት እንዲቀምሙ በማዘዝ በምስጢር ተሸሽጎ የመድኃኒቶቹን የቅመማ ሂደት ይከታተል ነበር።
በቀጣይ የ19ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ታሪክ እናነሳለን ።
ቸር ቆዩን!